የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት የዕለተ ቅዳሜ ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ
በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላሉ።
አ/አ ላይ በሚደረገው በቅዳሜ ብቸኛ የሊጉ ጨዋታ 10፡00 ሲል ኢትዮጵያ ቡናን ከ ፋሲል ከተማ የሚያገናኝ ይሆናል።
ሁለቱም ቡድኖች ከተደጋጋሚ ሽንፈቶች በኋላ በ13ኛው ሳምንት ወደ ድል የተመለሱ ሲሆን ዛሬ የሚያደርጉትንም ጨዋታ በማሸነፍ ደረጃቸውን ለማሻሻል እንዲሁም ሁለቱም ቡድኖች በመሀል ሜዳ ላይ ያተኮረ ጨዋታ የሚጫወቱ ቡድኖች ከመሆናቸው አኳያ ለተመልካች ማራኪ የሆነ ጨዋታ ያሳያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በ13ኛው ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ወደ ድሬ ተጉዞ ድሬዳዋ ከተማን በሳሙኤል ሳኑሚ እና አማኑኤል ዮሀንስ 2ግቦች ታግዞ 2-0 ያሸነፈ ሲሆን ፋሲል ከተማ በአንፃሩ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት የውጤት ቀውስ የሚገኘውን ኢትዮ-ኤሌክትሪክን አስተናግዶ በአብዱራህማን ሙባረክ(ግሪዳው) ብቸኛ ግብ 1-0 ማሸነፍ ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ፋሲል ከተማ ካደረጋቸው 13ጨዋታዎች 7ቱን ከሜዳው ውጪ ያደረገ ሲሆን ዛሬ ወደ አ/አ ተጉዞ የሚያደርገው ጨዋታ 8ኛ ከሜዳው ውጪ የሚያደርገው ጨዋታ ይሆናል፡፡ ፋሲል ከተማ ካደረጋቸው 7 ጨዋታዎች ወደ ጅማ ተጉዞ ጅማ አባጅፋርን እንዲሁም አ/አ ስታዲየም ላይ መከላከያን ሲያሸንፍ ከደደቢት ጋር አ/አ ስታዲየም እና አዳማ ላይ ከአዳማ ከተማ ጋር በተመሳሳይ ያለ ግብ 0-0 ድሬ ላይ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር 1-1 እንዲሁም አዲግራት ላይ ደግሞ ከወልዋሎ አ.ዩ. ጋር 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቶ ይርጋለም ላይ በሲዳማ ቡና 3-0 ተሸንፏል
በአጠቃላይ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ከ13 ጨዋታዎች 12 ጨዋታዎችን አድርጎ አራቱን በማሸነፍ ሶስቱን አቻ ወጥቶ በአምስቱ ተሸንፎ በ15 ነጥቦች 9ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል። ፋሲል ከተማ በአንፃሩ 13ጨዋታዎችን አድርጎ 4ጨዋታዎችን አሸንፎ 7ጨዋታዎችን አቻ ወጥቶ 2ጨዋታዎችን ተሸንፎ ማግኘት ከሚገባው 39ነጥቦች 19ኙን አሳክቶ ከተጋጣሚው በ4ነጥቦች ርቆ 6ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
ከኢትዮጵያ ቡና በኩል ሮቤል አስራት፣አለማየው ሙለታ እና ማናዬ ፋንቱ በጉዳት እማይኖሩ ሲሆን ። ከፋሲል ከተማ በኩል ያሬድ ባየህን እና አይናለም ሀይሉን በረጅም ጉዳት የሚያጣ ሲሆን ከሁለቱ ተጫዋቾች በተጨማሪ ዳዊት እስጢፋኖስ እና አብዱራህማን ሙባረክ(ግሪዳው)ን በጉዳት የሚያጣ ይሆናል፡፡
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ልክ 10:00 ሲል በ አ/አ ስታዲየም ላይ የሚጀምር ይሆናል።