የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት አካል የሆነው የጅማ አባጅፋርን እና ፋሲለ ከተማ ግጥሚያ እንደሚከተለው ከጨዋታ በፊት አንዳንድ ነጥቦችን አንስተንላቹሀል።
ጨዋታ : ጅማ አባ ጅፋር ከ ፋሲል ከተማ
የጨዋታ ቀን: እሮብ ጥር 20/5/2012
የጨዋታው ሰአት: 9:00 ሰአት
የጨዋታው አርቢትር:
የጨዋታ ቦታ: ጅማ ዩንቨርሲቲ ስታዲዮም
በወጣ ገባ አቋም ጉዟቸው እየቀጠሉ ለመተንበይ ከባድ የሆኑት ጅማ አባጅፋሮች ከሜዳው ውጭ ምንም አይነት ድል ማስመዘግብ ያቃተው ፋሲል ከተማን ጋብዞ ያስተናግዳል። ባለሜዳዎቹ ምንም እንኳን የመስመር አጨዋወታቸው ለተጋጣሚ ቡድን አደጋ ቢፈጥርባቸውም ተጋባዦቹ የመሀል ተከላካያቸውን የያሬድ ባየህ ከጉዳት ማገገም ጅማዎች በቀላሉ የግብ እድሎች ይፍጥራል ተብሎ አይጠበቅም። ግብ የማስቆጠር ምንም እንከን የማይታይባቸው አፄዎቹ የፊት መስመራቸው አስፈሪ ቢሆንም ከሜዳቸው ውጭ ያላቸው ጥንካሬ መሰረት በማድረግ እና የተጋጣሚያቸው የተከላካይ ስፍራ ጥንካሬ ግምት ውስጥ በማስገባት። ጠንካራውን የጅማ መከላከል መስበር ካልቻሉ የግብ አጋጣሚዎችን የመፍጠሩ ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚገባ ይሆናል። የሁለት ጨዋታዎችን ውጤት ስንመለከት ጋባዦቹ መግኘት ከነበረባቸው 6 ነጥብ 1 ብቻ ያሳኩ ሲሆን አፄዎቹ ደግሞ ከሚጠበቅባቸው 6 ነጥብ 3ን አግንተዋል።ፋሲል ከመሪው መቐለ 70 እንደርታ ላለመራቅ ጅማ አባጅፋሮች ደግሞ ከወራጅ ቀጠናው ለመራቅ የሚደረገው ይህ ጨዋታ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።
- ማሰታውቂያ -
በእርስ በእርስ ግንኙነት ፋሲል ከተማ ብዙ ግዜ በማሸነፍ የበላይነት አለው።