ወልዋሎ ከ ሀዋሳ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ታህሳስ 25/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር:
ቦታ: ትግራይ ስታድየም
ባሳለፍነው ሳምንት ደርቢ ጨዋታዎችን አካሂደው ሽንፈት ያስተናገዱት ወልዋሎ እና ሃዋሳ ከተማ ነገ በትግራይ ስታድየም ሚገናኙ ይሆናል።የሊጉ መሪ የሆኑት ወልዋሎዎች መሪነታቸውን ለማስጠበቅ ሀይቆቹ በበኩላቸው ከመሪዎቹ ተርታ ለመሰለፍ ጠንካራ ፋክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ቢጫ ለባሾቹ ወልዋሎዎች ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው አይናለም ሀይሉ፣በ3ተኛው ሳምንት ከስሁል ሽረ ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው አቼምፖንግ አሞስ፣ለዮውሃንስ ሳህሌ አጨዋወት አመቺ እንደሆነ ሚነገርለት ካርሎስ ዳምጠው በጉዳት ምክንያት ከነገው ጨዋታ ውጪ ሲሆኑ፤በደርቢው ጨዋታ በሁለት ቢጫ ከሜዳ የተሰናበተው ግብ ጠባቂው አብዱላዚዝ ኬይታ በቅጣት ሃይቆቹን ማይገጥም ይሆናል።በሃዋሳዎች በኩል ወጣት ተከላካያቸውን መሳይ ፖውሎስን መልሰው ሲያገኙ ቸርነት አውሽ በጉዳት አያሰልፋም።
መነሻቸው ከሁለቱን መስመሮች ባደረጉ ተሻሚ ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ሚሞክሩት ወልዋሎዎች በነገውም ጨዋታ ተመሳሳይ አቀራረብ ይዘው ሊገቡ እንደሚችሉ ይገመታል።በሊጉ የመጀመርያ ሥስት ጨዋታዎች ላይ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው ወጣቱ አጥቂ ሰመረ ሀፍታይ በነገው ጨዋታ ከኢታሙና ኩሜይኒ እና ጁንያንስ ናንጂቦ ጋር ሚኖራቸው ጥምረት የወልዋሎ ውጤት ማማር ላይ ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን የተሸነፋት ሃዋሳዎች በበኩላቸው ከሜዳቸው ውጪ እንደመጫወታቸው ጥንቃቄ ላይ መሰረት ያደረገ በወጣቶቹ አጥቂዎች ብሩክ በየነ እና መስፍን ታፈሰ ላይ ትኩረት ያደርገ አጨዋወትን ሊከተሉ እንደሚችሉ ይገመታል።