የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የክልል ጨዋታዎች ቅድመ ዳሰሳ ሐዋሳ ከተማ ከ ደደቢት፣ ሲዳማ ቡና ከ ውልዋሎ፣ፋሲል ከተማ ከ ጅማ አባጅፋር እና ድሬዳዋ ከተማ ከ ወልድያ የሚያደርጉትን ጨዋታወች በዚህ መልኩ ዳሰናቸዋል፡፡የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር አመቱ 18ኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ በሚደረጉ 6ጨዋታዎች የሚቀጥሉ ይሆናል። ከነዚህ 6ጨዋታዎች 4ቱ ክልል ላይ ሲደረጉ 2ቱ ደግሞ አ/አ ስታዲየም ላይ ይደረጋሉ።
ሀዋሳ ከተማ ከ ደደቢት
ዛሬ ከሚደረጉ 6ጨዋታዎች ሀዋሳ ላይ በ9 ሰዓት ሀዋሳ ከተማ ደደቢትን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ሀዋሳ ከተማ በ17ኛ ሳምንት መርሀግብር ከወልድያ ጋር 1-1 በሆነ የአቻ ውጤት ሲለያዩ መሪው ደደቢት በአንፃሩ አዳማ ከተማን ኤፍሬም አሻሞ ባገባት ብቸኛ ግብ 1-0 በማሸነፍ ለዚህ ጨዋታ ደርሷል፡፡
ሀዋሳ ከተማ በሜዳው የሚያደርጉትን ጨዋታወች በማሸነፍ እንዲሁም ከሜዳቸው ውጪ ደግሞ ደካማ ነጥብ በማስመዝገብ የውድድር አመቱን እያካሄደ ይገኛል፡፡ ደደቢት በአንፃሩ በሜዳውም ሆነ ከሜዳቸው ውጪ ነጥብ በማስመዝገብ የውድድር አመቱን ማጋመስ ችለዋል፡፡ ሁለቱ ክለቦች 11 ግዜ ተገናኝተው ደደቢት 5ግዜ ሲያሸንፍ ሀዋሳ 2ግዜ እንዲሁም 4 አቻ መውጣት ችለዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በሀዋሳ በኩል ምንም አይነት ጉዳትም ሆነ ቅጣት የለም፡፡ በደደቢት በኩል የቀኝ መስመር ተከላካዩን ስዮም ተስፋዬን በ5 ቢጫ ካርድ ምክንያት አያሰልፍም፡፡
የዛሬውን ጨዋታ በጨዋታው የተመደበው አርቢትር በአምላክ ተሠማ ነበር የሚመሪት ነገር ግን ዛምቢያ ላይ በሚደረግ የኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታ ላይ በመመደቡና የፊታችን ሃሙስ ወደስፍራው ስለሚጓዝ ጨዋታውን አርቢትር ቢኒያም ወ/አገኘሁ መመደቡ ታውቋል።
ሲዳማ ቡና ከ ውልዋሎ
አዲስ አሰልጣኝ የሾሙት ሁለቱም ክለቦች በሁለተኛው ዙር በሽንፈት በመጀመር ለዚህ ጨዋታ የደረሱ ሲሆን ከወራጅ ቀጠናው ለመዉጣት ፋልሚያ የሚያደርጉበት ጨዋታ ሲሆን ለተመልካች አጉዋጊ ይሆል።
አሰልጣኝ ዓለማየሁ አባይነህ ያሰናበተው ሲዳማ ቡና ሁለት ጨዋታዎችን በኳስ ቁጥጥሩ ብልጫ በመውሰድ እየቻለ በጥቃቅን ስህተቶች እየተሸነፋ ተገዱዋል ።
እንደ ሲዳማ ሁሉ ዋና አሰልጣኝ ብርሀኔ ገ/እግዚሀብሔር ያሰናበተው ዉልዋሎ ቀስበቀስ ዉጤት በማጣት ወደ ወራጅ ቀጠናው ተርታ መሰለፍ ችሏል።ሁለቱም ክለቦች መሸናነፋ ከቻሉ ከወራጅ ቀጠናዉ በጥቂቱም ቢሆን የሚርቁ ይሆናል።በሲዳማ በኩል ምንም አይነት ጉዳት ሆነ ቅጣት የለም፡፡ በወልዋሎ በኩል ደግሞ ግብ ጠባቂው በረከት አማረ በጉዳት ብርሀኑ አሻሞ በቅጣት የማይሰለፉ ይሆናል፡፡
ጨዋታውን አርቢትር ዳዊት አሳምነው ይመሩታል፡፡
ፋሲል ከተማ ከ ጅማአባጅፋር
ይህ ጨዋታ በ18 ሳምንት ክልል ከሚደረጉ 4ጨዋታዎች መካከል አንዱ ሲሆን በአፄ ፋሲለደስ ስታድየም የሚደረግ ይሆናል፡፡
ፋሲል ከተማ በቅዱስጊዩርጊስ አዲስአበባ ላይ 3-1 ሲሸነፍ፡፡ በተቃራኒው ጅማ አባጅፋር ጅማ ላይ በኦካኪ አፎላኒ ብቸኛ ግብ ማሸነፍ ችለዋል፡፡
ፋሲል የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ከመሪወቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት የሚያጠብ ሲሆን፡፡ይሄን ጨዋታ የሚሸነፉ ከሆነ ደጋፊዎች በአሰልጣኙ ላይ ተቃውሞ እንደሚያሰሙ ይጠበቃል፡፡ በአንፃሩ አባጅፋሮች ማሸነፍ ከቻሉ ከመሪው ደደቢት ያላቸውን ልዩነት የሚያጠቡበት እንዲሁም ተፅዕኖ የሚፈጥሩበት ይሆናል፡፡
በአንደኛው ዘር ተገናኝተው አፄዎቹ 1-0 ማሸነፍቸው ይታወሳል፡፡ጨዋታውን አርቢትር ኢብራሂም አጋዥ ሲመሩት፡፡በፋሲል ከተማ በኩል አብዱራህማን እና አይናለም ሀይሌ በጉዳት አይኖሩም፡፡ ጅማ አባጅፍር በኩል ምንም አይነት የጉዳትም ሆነ የቅጣት ዜና የለባቸውም፡፡
ድሬዳዋ ከተማ ከ ወልድያ
ጥሩ ያልሆነ አመትን ከሚያሳልፉ ክለቦች ውስጥ የሚገኝው ድሬደዳዋ ከተማ በደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ ላይ የሚገኝውን ወልድያ ከተማን ያስተናግዳል፡፡
ድሬዎቹ በ17 ሳምንት ወደ ጅማ ተጉዘው 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት ሽንፈትን ሲያስተናግዱ፡፡ ወልድያ ከተማ በሜዳቸው ከሀዋሳ ከተማ ጋር በተጨማሪ ሰዓት ምንያህል ተሾመ ባገባው ግብ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታውን ፈፅሟል፡፡
የዛሬው ጨዋታ በሁለቱም በኩል ተጠባቂ ሲሆን በተለይም ድሬዳዋ ከተማዎች በሜዳቸው እንደመሆናቸው መጠን አሸንፎ ለመወጣት ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡ ወልድያ ከተማዎች በአንፃሩ ከሜዳቸው ውጪ እንደመጫወታቸው መጠን መከላከል ላይ ያመዐነ ጨዋታ እንደሚጫወቱ ይጠበቃል፡፡
የጉዳት ዜና ስንመለከት በድሬዳዋ በኩል አሕመድ ረሺድና ጀማል ጣሰው እማይኖሩ ሲሆን በጅማ አባጅፋር በኩል እስከ ነገ ጨዋታ ድረስ አዲስ የጉዳት ዜና የለም
ጨዋታውን አርቢትር ዳንኤል ግርማይ ይመሩታል፡፡