በ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ሁለተኛ ቀን አንድ ጨዋታ ዛሬ ሲድረግ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ከፋሲል ከተማ ተገናኝተው ጨዋታቸውን 2-2 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል። ግብ በማግባቱ ረገድ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ቀዳሚ ሲሆን በ5ኛው ደቂቃ በሙሉዓለም ጥላሁን (ፍ.ቅ.ም) እንዲሁም 44ኛው ደቂቃ ላይ በከድር ሳለህ ያስቆጠሯቸው ግቦች መሪ መሆን ችሎ ነበር። ከእረፍት መልስ ፋሲል ከነማ 61ኛው ደቂቃ ላይ በሰኢድ ሀሰን እና 90ኛው ደቂቃ ላይ በአይናለም ሃይሉ ባስቆጠሯቸው ግቦች ከሜዳው ውጪ 1ነጥብ ይዞ መመለስ ችሏል።
ፕሪምየር ሊጉ ነገ(ሰኞ) ሲቀጥል ደደቢት ከ ወላይታ ዲቻ ማክሰኞ ደግሞ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከ መከላከያ በተመሳሳይ 11፡30 ሲል በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ ለብሔራዊ ቡድኑ 3 እና ከዛ በላይ ተጫዋቾችን ያስመረጡት ቅ/ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር የሚያደርጏቸው ጨዋታዎች ቀንና ሰዓት ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል፡፡
የፎቶው ምንጭ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ / fasil kenema football club ፌስቡክ ገጽ
በ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ወልዋሎ አ.ዩ የፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ነጥቡን አስመዘገበ፡፡
Editor at Hatricksport website