21ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ክለቦች ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል እየተሳተፈ የሚገኘው የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ወደ ወሳኙ የምድብ ድልድል ለመግባት የ90 ደቂቃ እድሜ ብቻ ቀርቶታል፡፡
በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 11:30 ሲል የጀመረው የሊዮፓርድ እእና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በ28ኛ ደቂቃ በምንተስኖት አዳነ ጎል አሸንፎ ሊወጣ ችልዋል፡፡በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ በ 80ኛ ደቂቃ ላይ የጨዋታው ጎል አስቆጣሪ ምንተስኖት አዳነን በሁለት ቢጫ ከሜዳ አሰናብተዋል፡፡
በጨዋታው ሂደት የዳኛ ውሳኔ ላይ ሰፊ የአመራር ችግር እንደነበር ተውቋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድሩ ቅድመ ማጣሪያ የሲሸልሱን ሻምፒዮን ኮት ዲኦርን በሳላዲን ሰኢድ (3)፣ አስቻለው ታመነ እና በሀይሉ አሰፋ ጎሎች በድምሩ 5ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፎ ወደዚህኛው ዙር ያለፈ ሲሆን ተጋጣሚው ኤሲ ሊዮፓርድስ በበኩሉ የካሜሮኑን ዩ ኤስ ኤም ዴሉምን በሜዳው 1ለ0 አሸንፎ ከሜዳው ውጭ ደግሞ 2ለ1 ተሸንፎ ነገር ግን ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ህግ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የበቃ ነው፡፡ የሁለቱ ቡድኖች የደርሶ መልስ ጨዋታ በሳምንት ጊዜ ልዩነት ውስጥ የሚከናወን ሲሆን የሁለቱ ጨዋታዎች የደርሶ መልስ አሸናፊ በውድድሩ ምድብ ድልድል ውስጥ መግባት እና ከሌሎች 3 ክለቦች ጋር በደርሶ መልስ የመጫወት እድልን ከማግኘቱ በተጨማሪ የአምስት መቶ ሀምሳ ሺህ ዶላር ወይም ወደ አስራ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ብር ተሸላሚም ይሆናል፡፡ ተሸናፊው ቡድን በአንፃሩ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል ውስጥ ለመግባት ከሌላ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ ቡድን ጋር በደርሶ መልስ የመጫወት እድል የሚኖረው ሲሆን ወደ ምድብ ድልድሉ የሚያልፍ ከሆነም የቻምፒዮንስ ሊጉን ያክልም ባይሆን ጠቀም ያለ የገንዘብ ሽልማት አብሮ የሚበረከትለት ይሆናል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚ ኤሲ ሊዮፓርድስክለቡ እ.ኤ.አ በ1953 ዓ.ም የተመሰረተ እና ሙሉ ስሙ አትሌቲክ ክለብ ሊዮፓርድስ ሲባል በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዴኒስ ሳሱ ኒጉኤሶ ስም የተሰየመ 5000 ተመልካቾችን ማስተናገድ የሚችል ስታዲየም ባለቤት ነው፡፡ ምንም እንኳን ክለቡ ረዥም የምስረታ እድሜ ቢኖረውም የውጤታማነት ታሪኩ ግን በቅርብ አመታት የተመዘገቡ እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተለይም እ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ዓመታት ክለቡ ያለዋንጫ ያጠናቀቀበትን የውድድር ዓመት ማግኘት ከባድ ነው፡፡ በታሪኩ ያስመዘገባቸውን 3 የኮንጎ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊነት፣ 5 የኮንጎ ዋንጫ እና በ2012 ያሳካውን የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ድሎች ያገኘው ከላይ ከተጠቀሰው ዓመት ወደዚህ መሆኑን መመልከትም የክለቡን የቅርብ ጊዜያት ተከታታይ ውጤታማነት ማረጋገጫ ነው፡፡ የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ የፊታችን ሳምንት እሁድ መጋቢት 10/2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት እንደሚከናወን ተረጋግጧል፡፡