በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ዛሬ የምድቡን አምስተኛ ጨዋታ ያደረገው የኢትዮጵያ ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ሳይቀናው ከምድቡ ተሰናብቷል
በጨዋታው ኳስን ያስጀመሩት ሰንዳውንሶች ሲሆኑ ጨዋታው በተጀመረ በአራተኛው ደቂቃ ላይ በሃይሉ አሰፋ ከመስመር ያሻገረውን ካስ የሰንዳውንስ ተከላካይ ኳስ ለማውጣት ሲሞክር የመታው ኳስ የግቡን አግዳሚ ገጭቶ ሲወጣ ብዙም ሳይቆይ በ6ኛው ደቂቃ ኒኪማ ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጭ ወጥቷል።
ፈረሰኞቹ በመጀመሪያው 10ደቂቃዎች ውስጥ በጨዋታው ግልፅ የበላይነትን ወስደው ታይተዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በዛሬው ጨዋታ ላይ የሰንዳውንስ ግብ ጠባቂ እና የወቅቱ የአፍሪካ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ዴኒስ ኦኒያንጎ ሲሆን የቀድሞ ክለቡን ገጥመዋል ። ዴኒስ በ1998 ላይ የፈረሰኞቹ የቡድን አባል እንደ ነበር እሚታወስ ነው።
ፈረሰኞቹ በጨዋታው የበላይነት መውሰድ የቻሉት ለ30ደቂቃዎች ብቻ ነበር፡፡
ጨዋታው ሊጠናቀቀ የአንድ ደቂቃ የባከነ ሰዓት ባሳዩበት አልጄሪያዊው አራተኛ ዳኛ:ቀመቅፅበት የሰንዳውንስ ተጨዋቾች ኳስ በእጅ በመነካቱ የጨዋታው የመሃል ዳኛ የፍፁም ቅጣት ምት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጥተዋል።ፈረሰኞቹ ያገኙትን አጋጣሚ የፍፁም ቅጣት ምቱን የፊት መስመር ተጨዋቾች ሳላሃዲን ሰይድ መትቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።በዚሁም የጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡
በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ቅዱስ ጊዮርጊሶች የጨዋታው ኳስ ሲያስጀምሩ። በ49ኛውደቂቃ ላይ ፕሪንስ ከግቡ ግራ መስመር እያጠበበ ገብቶ ወደ ጎል የሞከራት ኳስ ወደ ውጪ ወጧል።
በሁለተኛው የጨዋታው አጋማሽ ሰንዳውንሶች የአቻ ውጤቱን የፈለጉት በሚስል በተደጋጋሚ ኳሶችን ሲያዘገዩ ተያተዋል።
በሰንዳውንሶች በኩል በጨዋታው 56 ደቂቃ በአንድ ሁለት ቅብብል ይዘው የገቡትን ኳስ በሮበርቶ ኦድንካር ድንቅ ብቃት ከሽፏል ።
ሰንዳውንሶች ከ60ኛው ደቂቃ በኃላ የቅዱስ ጊዮርጊስ የአማካይ ክፍል መዳከምን ተከትሎ በተደጋጋሚ ጊዜ በግራ እና ቀኝ መስመሮች ጥቃት በማድረስ የተሳካላቸው ነበሩ ። በዚህም በሶስት ደቂቃዎች ውስጥ ሁለት የማዕዘን ምቶችን ሊያገኙ ችለዋል ።
ፈረሰኞቹ የመጀመሪያውን የተጫዋች ቅያሪ ያደረጉት በ64ኛ ደቂቃ ላይ ሲሆን አዳነ ግርማን በፕሪንስ ቀይረው ወደሜዳ አስገብተዋል ።አዳነ ግርማ በገባ በሁለት ደቂቃዎች ልዩነት ከርቀት የሞከሩት ኳስ በሮበርት ድንቅ ብቃት ሊመለስ ችሏል።
በ76 ኛ ደቂቃ ላይ አብዛኛውን የእግርኳስ ተመልካቾች አነጋጋሪ ቅያሪ ያደረጉት ፈረሰኞቹ በሃይሉ አሰፋን በየሲር ሙገርዋ ቀይረዋል ።
በ ሰንዳውንሶች በኩል የጨዋታው መገባደጃ ደቂቃዎች ላይ ከራሳቸው የግብ ክልል ተጠግተው እየተጫወቱ ይገ። ፈረሰኞቹ ለማስከፈት ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርጉ ለመታዘብ ተችሏል፡፡
በፈረሰኞቹ አሰልጣኞች የማጥቃት ጫናን ለማሳደር በሚመስል መልኩ 3ኛውን የተጨዋች ለውጥ የመስመር ተከላካዩን ፍሬዘር ካሳንን ቡሩኖ ኮኔ ቀይረው ወደሜዳ አስገብተዋል።
በ85ኛው ደቂቃ ላይ ሰንዳውንሶች የጊዮርጊስ ተከላካዮች የፈጠሩትን ስህተት ተጠቅመው በላፎር ጎል አስቆጥረዋል
ከጎልዋ መቆጠር ሰንዳሳውንሶች አፈግፍገው የበለጠ በመከላከል ጨዋታውን አሸንፈው ሊወጡ ችለዋል።
የአሰልጣኞች አስተያየት
ፋሲል ተካልኝ ቅዱስጊዮርጊስ አሰልጣኝ
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ የፈጠረናቸውን የጎል አጋጣሚዎች ሳንጠቀምባቸው መቅረታችን እሚያስቆጭ አጋጣሚ ነው፡፡ ጨዋታውን የመሸነፋችን በፔናሊቲው መሳት ማሳበብ አልፈልግም፡፡በሁለተኛው አጋማሽ ያደረግናቸው የተጫዋቾች ቅያሪ በይበልጥ ለማጥቃት አስበን ያደረግነው ነው፡፡ ጊዮርጊስ ከልጅነቴ ያደጉበት ክለብ ነው በውጤቱ በጣም አዝኛለሁ ፤ውስጤ ደምቷል
ፒትሶ ሞሲማኔ የሜማሎዲ ሰንዳውንስ
መጀመሪያ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ያሳዮት የአደጋገፍ ሆኔታ በጣም እሚያምር ነበር ይሄ ድባብ ቡድኔ ቢኖረው ኖሮ ሙሉለሙሉ ይቀየር ነበር፡፡ የዚህ አይነት የአደጋገፍ ስልት እኔ ቡድን ውስጥ እንዲኖር እመኛለሁ፡፡