ባለፋት ዓመታት ሁለቱ ቡድኖች በሚገናኙበት ጊዜ እየተለመደ የመጣውን የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለትን ለማስቀረት ታስቦ በእዳማ እበበ በቂላ ስታድየም የሀገር ሽማሌዎች፣የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ ና የሁለቱ ክለብ አመራር ተወካዮች እንዲሁም ደጋፊዎች በተገኙበት የእርቀ ሰላም ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አባላትና ደጋፊዎች ከ አዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች የእርስ በርስ ወዳጅነትን የማጠንከር፣ ያለፉ ችግሮችን የመፍታትና እርቅ ፕሮግራም በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎችና አመራሮች፣ አባ ገዳዎች እና የሚዲያ አካላት በተገኙበት ተካሄደ።
“በሁለቱ ክለቦች መካከል ቀድሞ የነበረውን መልካምና የጠነከረ ግንኙነት ጥቃቅን በሚባሉ ምክንያቶች እና ስህተቶች ደፍርሷል። ይህን የደፈረሰውን ሰላም በአዲስ መንፈስ ለማጥራት፣ ለማስቀጠልና ለሌሎች ክለቦች ዓርዓያ ለመሆን ያስችል ዘንድ ሁላችንም ኃላፊነት መወጣት አለብን፤ እግር ኳሳችን በደጋፊዎች ሁከት መበጥበጥ የለበትም።”
የሚሉ መልዕክቶች በፕሮግራሙ ላይ ተላልፈዋል።
source- የቅዱስ ጊዮርጊስ ይፋዊ ገፅ