በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) የሚወጣው ወርሃዊው የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ ይፋ ሆኗል።
ፊፋ ባወጣው የወሩ ደረጃም ብራዚል 1ኛ ስትሆን አርጀንቲና ከባለፈው ወር አንድ በመቀነስ ሁለተኛ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ጀርመን ደግሞ የባለፈውን ሶስተኛን ደረጃ አልለቀቀችም፡፡
ኢትዮጵያም በወንዶች ባለፈው ወር ከነበረችበት 20 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል ከ103ኛ ወርዳ 124ኛ ላይ ተቀምጣለች።
- ማሰታውቂያ -
ከአፍሪካ ግብፅ ቀዳሚ ስትሆን ሴኔጋል እና የወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮን ካሜሩን ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።
በወሩ ላይቤሪያ 39፣ ኪቲስና ኔቪስ 26 እንዲሁም ሩዋንዳ 24 ደረጃዎችን የቀነሱ ሀገራት ሲሆኑ፥ መቄዶንያ 33፣ ህንድ 31 እና የመን በ25 ደረጃዎች ከፍተኛ መሻሻል አሳይተዋል።