ምንተስኖት አሎን ለመከላከያ አሳልፎ የሰጠው ባህርዳር ከተማ ፅዮን መርዕድን የግሉ አድርጓል።በከፍተኛ ሊጉ ከአርባምንጭ ጋር ቆይታ ያደረገው ፅዮን መርዕድ የፋሲል ተካልኝ የክረምቱ አምስተኛ ፈራሚ ሆኖ ባህርዳርን ተቀላቅሏል።
ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ልምምድ ጀምሮ የነበረው ፅዮን በተለያዩ ምክንያቶች አለመስማማቱን ተከትሎ ለጣና ሞገዶቹ ሊፈርም ችሏል።
ለኢትዮጵያ ወጣት ብሄራዊ ቡድን መጫወት የቻለው ፅዮን መርዕድ በባህርዳር የቀዋሚ ተሰላፊነት ዕድል ለማግኘት ከሃሪሰን ሄሱ ጋር ሚፎካከር ይሆናል።