በመሸሻ ወልዴ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአማካይ
ስፍራ ተጨዋች ከነዓን ማርክነህ
ዋልያዎቹ ዘንድሮ በሚያደርጓቸው
የአፍሪካ ዋንጫ እና የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ
ጨዋታዎች ዋንኛው እቅዳቸው ጥሩ
ውጤት ማምጣት እና ሀገራቸውን በታላቅ
የውድድር መድረክ ላይ ማብቃት መሆኑን
ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ10 ቀናቶች
በኋላ ለሚያደርጋቸው የአፍሪካ ዋንጫም
ሆነ የተለያዩ የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ወደ
መቀለ በመጓዝ የቅድመ ዝግጅቱን መስራት
በጀመረበት የአሁን ሰዓት ከነዓን ማርክነህን
ተደጋጋሚ ሽንፈትን ስላስተናገደው
የብሔራዊ ቡድናችን እንደዚሁም ደግሞ
ዋልያዎቹ ከዚህ በኋላ የተለያዩ ውድድሮች
ላይ በምን መልኩ እንደሚቀርቡና ሌሎችንም
ከእሱ ጋር የሚያያዙ ጥያቄዎችን አቅርበንለት
በሚከተለው መልኩ ምላሹን ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን /
ዋልያዎቹ/ ተደጋጋሚ ሽንፈቶችን እያስተናገደ
ይገኛል፤ ይሄ የውጤት ማጣት ችግር ከምን
መጣ? ቡድኑ አሁን ላይ ያለበት አቋምና
ደረጃስ ምን ይመስላል?
ከነዓን፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
ከቅርብ ጊዜያቶች ወዲህ በአፍሪካ
ዋንጫና በተለያዩ የማጣሪያ ጨዋታዎች
ላይ ተደጋጋሚ የውጤት ማጣትንና
ሽንፈቶችን እያስተናገደ የሚገኝበት ዋንኛው
ምክንያት የመጀመሪያው የሊጉ በተደጋጋሚ
ጊዜ መቋረጥ የየክለቡን ጥሩ ጥሩ የሆኑ
ተጨዋቾችን በወቅታዊ ጥሩ አቋማቸው
ላይ እንዳይገኙ ስለሚያደርጋቸው እነዛን
ተጨዋቾች ለብሔራዊ ቡድናችን መመረጡ
ላይ የሚያስቸግርበት ሁኔታ ስላለ ከዛ
ውጪ ደግሞ ቡድኑ በወጣት ተጨዋቾች
ከመገንባቱ አኳያ የልምድ ማነስ ችግር
ስላለበት እነዛ ለውጤት ማጣታችን በጣሙን
ሊጎዱን ችለዋል፡፡ ስለዚህም የአሁን ሰዓት
ላይ በአጨዋወት በኩል አበረታችና ጥሩ
እንቅስቃሴ እያሳየ ያለው ይኸው ቡድን
በጎል ማስቆጠሩ ላይ ከፍተኛ የአጨራረስ
ችግርና ድክመት ያለበት በመሆኑ ወደ
ውጤታማነት ልናመጣው ይገባል፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን
የአሁን ሰዓት ላይ በምን መልኩ ወደ
ውጤታማነት ማምጣት ይቻላል?
ከነዓን፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
ከቅርብ ጊዜያቶች ወዲህ በተለይ ደግሞ
ሩዋንዳን በተፋለመበት የቻን የአፍሪካ
ዋንጫ የማጣሪያ ግጥሚያ ላይ ጥሩ የሜዳ
ላይ እንቅስቃሴን ስላሳየን ለወደፊቱ
የውጤት ማምጣት የምናስብ ከሆነ ያ
ግጥሚያ ለእኛ ትልቅ መማሪያ ሊሆነን
ይገባል፤ በተለይ ደግሞ ያን የያዝነውን
አጨዋወት የማንለቅ ከሆነና ከዛ
ውጪም ቡድኑን ሊያጠናክሩ የሚችሉ
ሌሎች ተጨማሪ ተጨዋቾች
የሚመጡበት ሁኔታ ከተፈጠረ
እንደዚሁም ጎል ማስቆጠሩም ላይ
ያለብንን ክፍተት አስተካክለን
የምንመጣ ከሆነ
የውጤታማነቱን ስኬት
በአጭር ጊዜ ውስጥ
እናመጠዋለን፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮ
ጵያ ብሔራዊ ቡድንን
የአሁኑ የተጨዋቾች
ስብስብ በምን መልኩ ነው የምት ገልፀው?
ከነዓን፡- የአሁኑ የዋልያዎቹ የተጨዋቾች
ስብስብ በወጣቶች የተገነባና ብዙም ተስፋ
ሰጪ ችሎታ ያላቸውን ተጨዋቾች ያሰባሰበ
ስለሆነ በአሁን ሰዓት ስኳዱን በጥሩ መልኩ
ነው የምገልፀው፤ ይሄ ቡድን አሁን ልምድ
ነው ያጣው፤ ወደፊት ቡድኑን የሚያጠናክሩ
ልምድ ያላቸው ሌሎች ተጨዋቾች
ሲጨመሩበት ደግሞ በውጤታማነት ደረጃ
ብዙ የምንጓዝ ይመስለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
ከመጪዎቹ ሳምንታቶች አንስቶ የተለያዩ
የአፍሪካና የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ
ግጥሚያዎችን ያደርጋል፤ በውድድሩ
ተሳትፎአችሁ ምን ውጤቶችን ለማስመዝገብ
ነው እየተዘጋጃችሁ የሚገኘው?
ከነዓን፡- የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ
ማሸነፍ መሸነፍና አቻ መውጣት ያለና
የሚኖር ቢሆንም በአሁን ሰዓት እኛ
የዋልያዎቹ የተጨዋቾች ስብስብ ከቅርብ
ጊዜያት ወዲህ በምናደርጋቸው የተለያዩ
የማጣሪያ ጨዋታዎች እንደ ማንኛውም
ሀገር ውጤታማ ሆነን
ሀገራችንን ለታላቅ
የውድድር መድረክ ለማ
ብቃት በጥሩ ሁኔታ
እየተዘጋጀን ነው የም
ንገኘው፤ በተለይ
ደግሞ የአሁኑ ቡድን
የሚጎለውን ነገር ያወቀ
ስለሆነም በቀጣይነት ጥሩ
ውጤት የምናመጣም
ይመስለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ቡድን በማጣሪያ
ጨዋታው የተደለደለው
እኮ እንደ እነ ኮትዲቯርና
ከመሳሰሉ ሀገራት ጋር
ነው…. አንተ ግን ከእነዚህ
ጋር ተጫ ውተን ጥሩ
ውጤት እናመጣለን፤
ለአፍሪካም ዋንጫም
እናልፋለን እያልክ ነው፤ ያ የሚሳካ ይመስ
ልሃል?
ከነዓን፡- አዎን፤ ኮትዲቭዋር በእግር
ኳሱ ትልቅ የሆነች ሀገር እና ከእኛም በጣም
የተሻለች ነች፤ እንደዛ ስለሆነች ግን እሷን
ኳስ ከመሆኑ አኳያ ሁሉም ነገር በሜዳ ላይ
እና በወቅታዊም አቋም የሚወሰን ስለሆነ
በጣም የምናከብዳት እና የምናገዝፋት ነገር
የለምና ብዙ ጊዜ ደግሞ እንደምንሰማውና
እንደምንመለከተው ትላልቅ ቡድኖች
በትናንሽ ቡድኖች የሚሸነፉበት ነገርም አለና
እነ ኮትዲቭዋርን የመሳሰሉት ሀገር ጋር
ስንጫወት አክብረናቸው ወደ ሜዳ በመግባት
ጥሩ ውጤት እናመጣለን ብዬ አስባለው፡፡
ሀትሪክ፡- እንደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
ተጨዋችነትህ አሁን ላይ በምትፈልግበት
ደረጃና አቋም ላይ ነው የምትገኘው?
ከነዓን፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነቴ
አሁን ላይ በምፈልገው ደረጃም ሆነ አቋም
ላይ እገኛለው ብዬ ፈፅሞ አላስብም፤ በኳስ
ብቃቴ ላይ ብዙ የማስተካክላቸው ነገሮች
አሉ፤ እነዛንም ከአሰልጣኞቼ ጋር ተነጋግሬና
ጠንክሬም ሰርቼበት ወደፊት ጥሩ ደረጃ
ላይ መድረስን እፈልጋለው፤ በኳሱ ላይ
ባለኝ ወቅታዊ አቋም ዓምና ከጉዳት ጋር
በተያያዘ ስጫወትም ሳልጫወትም ነበር ይሄ
በመሆኑም ራሴን ሳላገኘው ቀርቻለው፤
ዘንድሮ ግን አቋሜን በሚገባ አስተካክዬ
በመቅረብ ለክለቤም ሆነ ለሀገሬ ብሄራዊ ቡድን
ጥሩ ለመጫወትና ውጤታማም ለማድረግ
እንደዚሁም ደግሞ ካለፈው ዓመት አንስቶ
ወደ ውጪ ሀገር በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
ወጥቶ መጫወት የጀመርኳቸውን
ፕሮሰሶች ለማሳካት ጠንክሮ መስራቱ
ላይ ዝግጁ ሆኛለውና በእዚህ ዓመት
ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በጥሩ
አቋም ላይ የምገኝ ይመስለኛል፡፡
ሀትሪክ፡-
በመጨረሻ……….?
ከነዓን፡- የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ቡድንን
በሚመለከት እና ስለራሴ
ቡድንም አዳማ ከተማ
አንድ ነገር ብል
ደስ ይለኛል፤ አዳማ
ከተማ በዘንድሮ
የሊጉ ውድድር ዓምና
ካስመዘገበው ውጤት
በተሻለ መልኩ አንሰራርቶ ጥሩ
ውጤት እንዲያመጣ የሚቻለኝን
ሁሉ አደርጋለው፤ ቡድናችን ለእዛ
ሲል ደግሞ ቀድሞ ውጤታማ
ያደረገውን አሰልጣኝ ወደ ክለቡ
መልሶ የአሁን ሰዓት ላይ በጥሩ
መልኩ የፕሪ ሲዝን ዝግጅቱን
እየሰራ ይገኛል፤ ክለባችንን
ከማጠናከርም አኳያ ጥሩ
ጥሩ የሆኑ ተጨዋቾችም
እኛን ተቀላቅለዋልና
የቀድሞውን ጠንካራና
አስፈሪውን አዳማ ከተማን
የምናስመለክታችሁም
ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ
ቡድንን በተመለከተ ደግሞ
ወደፊት በምናደርጋቸው
የተለያዩ የማጣሪያ
ጨዋታዎች ላይ እኛ
የዋልያዎቹ ስብስብ
ሀገራችንን ለጥሩ
ውጤት
በማብቃት እና
የሀገራችንንም
የእግር ኳስ
አፍቃሪዎች
ለማስደሰት እየተዘጋጀን ይገኛ
ልና ለዛ ፈጣሪ ይርዳን እላለሁ፡፡