_________________________________
ባለፋት ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች ያልተካሄደው ትግራይ ዋንጫ በያዝነው ዓመት በትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ሽቶ ሚድያ እና ኣድቨርታይዝመንት ኣዘጋጅነት ከመስከረም 18-26 እንደሚካሄድ ዛሬ ፕላኔት ሆቴል ላይ በተሰጠው ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጽዋል።ኣምስት የትግራይ ክልል ክለቦች(መቐለ ከተማ፣ወልዋሎ ዓ.ዩኒቨርሲቲ፣ደደቢት፣ሽረ እንዳስላሴ፣ኣክሱም ከተማ) እንዲሁም 3 ተጋባዥ ክለቦች መካከል ይካሄዳል።ከሦስቱ ተጋባዥ ክለቦች መቐለ ላይ ቅድመ ውድድር ዝግጅት(pre season ) እያደረገ ሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም መከላከያ ውድድሩ ላይ እንደሚሳተፋ የተረጋገጠ ሲሆን ሥስተኛው ተሳታፊ ክለብ ለማግኘት ለፋሲል ከተማ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ኣዳማ ከተማ፣ሲዳማ ከተማ ግብዣ የቀረበላቸው ሲሆን ከ ኣራቱ ክለቦች ኣንዱ ውድድሩ ላይ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።