በፌዴሬሽኑ የህዝብ ኮሚኑኬሽን ሃላፊ ባህሩ ጥላሁን አስተባባሪነት በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተነሱት አንኳር ነጥቦች በዚህ መልኩ አዘጋጅተናል።
አብርሃም መብራህቱ ያነሱዋቸው ነጥቦች
የተደረገላቸው አቀባበል በተመለከተ
” አርብ ማታ ነበር መቐለ የገባነው ስንገባም በመቐለ 70 አንደርታ ደጋፊዎችና በትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካኝነት ደማቅ አቀባበል ተደርጎልናል በአቀባበሉም በጣም ደስተኞች ነን።
- ማሰታውቂያ -
ለጨዋታው ስላደረጉት ልምምድ
“ልምምዳችን የጀመርነው ቅዳሜ ነበር፤በመጀመርያ ቀን ልምምዳችን ቀለል ያለ ልምምድ ሰርተናል።መደበኛ ልምምዳችንን አሁድ ነው የጀመርነው ባጠቃላይ ስድስት መደበኛ ልምምዶች እና ሁለት ቀላል ልምምዶችን ሰርተናል።
ያረፋበት ሆቴል መስተንግዶ በተመለከተ
“ያረፍንበት አክሱም ሆቴል ከዚህ ቀደምም የእግር ኳስ ክለቦችን በማስተናገድ ልምድ ያለው ስለሆነ ሆቴሉን ምርጫችን አድርገናል። እየተደረገልን ባለው መስተንግዶም በጣም ደስተኞች ነን ።
የመጫወቻ ሜዳው በተመለከተ
” በመጀመርያ አካባቢ ሳሩ ባለመታጨዱ ምክንያት ልምምድ ለማድረግ ተቸግረን ነበር።ከዛም የትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የስታድየሙ ጠባቂዎችን አናግረን ሳሩ ሊታጨድ ችሏል። ሆኖም ሳሩ እስኪታጨድ ድረስ የቅድመ ዝግጅታቸውን ነው መቐለ ላይ እያደረጉ ሚገኙት መቐለ 70 አንደርታና ወልዋሎ ባደረጉልን ትብብር ልምምዳችን ሳይስተጓገል ማድረግ ችለናል።
ለነገው ጨዋታ ማይደርሱ ተጨዋቾች በተመለከተ
” ጀማል ጣሰው በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ከነገው ጨዋታ ውጪ ነው፤በተጨማሪ ሱራፋኤል ዳኛቸው በካፍ ህግ መሰረት ባለፋት ጨዋታዎች ባያቸው ቢጫ ካርዶች ምክንያት፣ፍፁም አለሙ የፓስፖርት ፕሮሰስ አለማለቁ ተከትሎ ከነገው ጨዋታ ውጪ ናቸው።
የቡድኑ አምፐል አስቻለው ታመነ
የተደረገላቸው አቀባበል በተመለከተ
“መቐለ ስንደርስ በተደረገልን አቀባበል በጣም ደስተኞች ነን።ህዝቡ ኳስ አፍቃሪ መሆኑን እናቃለን ነገም ስታድየም ገብቶ ድጋፍ አንደሚሰጠን እርግጠኛ ነን።
ቡድኑ ላይ ያለው መንፈስ እና መነሳሳት በተመለከተ
ቡድናችን ላይ ጥሩ መንፈስ እና መነሳሳት አለ።ከሌሴቶ ነጥብ ይዘን መምጣታችን እና ወደ ምድብ ድልድል መግባታችን ቡድናችን ላይ ጥሩ መንፈስ እና ተነሳሳሽነት አንዲኖር አግዞናል።
ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች እና በአሰልጣኙ የተሰጡ ምላሾች
ግብ ማስቆጠር ላይ ያላችሁን ችግር ለመቅረፍ ያደረጋችሁት ዝግጅት ካለ?የተጋጣሚ ቡድን አጨዋወት ለማጥናት የሄዳችሁት መንገድ ካለ?
“ለጥያቄዎቹ አመሰግናለው። ሁላችሁም በተደጋጋሚ አንደምታነሱት ተጋጣሚ ቡድን ላይ ብልጫ እየወሰደ ነገር ግን ግብ የማግባት ችግር አለበት ይሄ ትክክል ነው።ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት መቐለ ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ ግብ በማስቆጠር(finishing) ስራዎች ላይ የምንችለው ያህል ሰርተናል።አዚህ ላይ መጥቀስ ምፈልገው ነገር ምንድነው ግብ የማግባት ችግሩ ብሄራዊ ቡድኑ ላይ ሚንፀባረቀው መሰረቱ ክለብ ላይ ብዙ ስላልተቀረፈ ነው።ከጊዜ ወደ ጊዜ አጨራረስ ላይ ያለንን ድክመት ካላሻሽልልን እና ካላስተካካልን በስተቀር ዋጋ እያስከፈለን ነው ሚሄደው።በትሬኒንግ ደግሞ የሜዳ ተጣቃሚነታችንን(home advantage) ለመጠቀም ካስፈለገ ግብ ማስቆጠር በጣም አስፈላጊ ነውና በዛ ላይ ሳምንቱን ሙሉ ስፔሻል ልምምዶችን እየሰጠን ሰርተናል።የሩዋንዳን ቲም በተመለከተ የሩዋንዳ ቲም ምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ጠንካራ ከሚባሉ ሃገሮች አንዱ ነው።በቅርብ ያለን መረጃ እኛ ከሌሴቶ ጋር ስንጫወት እነሱ ደሞ ከሲሸልስ ጋር ያደረጉትን የደርሶ መልስ ጨዋታ አይተን ጥሩ ቡድን አንደሆነ አይተናል።ነገር ግን ልክ አንደኛ ከግብፅ እና ስዊድን ያመጣናቸው ልጆች አንደማይሳተፋ ሁሉ ሲሸልስን ከገጠመው የሩዋንዳ ስብስብ አራት ተጨዋቾቻቸው አይሳተፋም።ሆኖም ግን ጠንካራ ቡድን ሆኖ አንደሚቀርብ ይገመታል።ስለዚህ ከዚህ አንፃር ይህኑን መረጃ መሰረት በማድረግ የራሳችንን ዝግጅት አድርገናል።ቪድዮውንም ከተጨዋቾቼ ጋር በድምብ ተመልክተናል እና የራሳችንን ዝግጅት አድርገናል።ሌላው የሩዋንዳ ቡድን አዲስ አበባ ከመምጣቱ በፊት ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር የወዳኝነት ጨዋታ አድርጓል።ያንን ጨዋታ የናንተን መሰል ሞያተኞች ከፃፍዎቸው የፈረንሳይኛ ቋንቋ ፅሁፎች በስተቀር በፊልም የተደገፈ መረጃ ማግኘት አልቻልንም።ነገር ግን የወዳጅነት ጨዋታውን 3ለ2 አሸንፈው መምጣታቸው መረጃ አለ።እና ይሄ ሚያሳየው ምንድን ነው ቡድኑ ራሱን ለማቀናጀት ከጨዋታ ጨዋታ የወዳጅነት ጨዋታዎችን እያደረገ ራሱን እየፈተሸ የመጣ ቡድን ነው።የኛ በተቃራኒው ደሞ ምንም የወዳጅነት ጨዋታ ሳያገኝ ነው የቀረበው።ስለዚህ ያንን በወዳጅነት ጨዋታዎች ያጣናቸውን ክፍተቶች አዚ መቐለ ከመጣን በኃላ ባደረግናቸው የእርስ በርስ ጨዋታዎች ለመዝጋት ጥረት አድርገናል።
ስለፍፁም የፓስ ፖርት ጉዳይ እና በአሰልጣኙ ውል ላይ ስለተካተተው ለቻን ውድድር ብቁ ቡድን የመስራት ሃላፊነት የተሰጠው መልስ
“ከፓስፖርት ችግር ወይም ከጉዞ ሰነዶች ጋር ተያይዞ አንዳንድ ችግሮች ይስተዋላሉ።አብዛኞቹ ችግሮች አየተቀረፋ ይገኛሉ።ከፌዴሬሽኑ ጋር በቅንጅት እየሰራን ጥሩ እየሄደ ነው።የፍፁም ግን ምንድነው ቀደም ሲል ሲታወቅበት ከነበረው ኤፍሬም ስሙን ስለቀየረ ከሱ ጋር ተያይዞ ለማስተካከል ጊዜ ስለወሰደ ብቻ ነው አንጂ ከፌዴሬሽኑ በኩል ጥሩ ትብብር እየተደረገልን ነው።ግን ያም ሆኖ ይሄንን አንደ ትምህርት ወስደን በቀጣይ ያለምንም አንከን ከጉዞ ሰነድ ጋር ከፓስ ፖርት ጋት የተያያዙ ችግሮች ጊዜው ሳይደርስ መፈታት አንዳለባቸው በጣም ጥሩ ጥቆማ ነው ተቀብለናል።ሌላው አንግዲ ከፌዴሬሽኑ ጋር በነበረን ስምምነት መሰረት ለቻን 2020 ጠንካራ ቡድን ይዞ ለመቅረብ ነበር።ያንን ስንስማማ ሃገራችን ላይ ይካሄዳል በሚል ነበር በአጋጣሚ ግን አዘጋጅነታችን ስንነጠቅ አነዚህ ሁለት ውድድሮች ነበሩ።ስለዚህ አንደ አሰልጣኝ ለሁሉም ውድድር ዝግጁ መሆን ይጠይቃል።ስለዚህ ተቀያያሪ(flexible) መሆን ያስፈልጋል።ስለዚህ በዛ መሰረት አንግዲ በድንገት የመጣውን የጁቡቲ ጨዋታ በደርሶ መልስ በጥሩ ውጤት ተወጥተናል።ከዛ በኃላ ደግሞ ቅድም ያነሳሁት የሌሴቶ ጨዋታ በደርሶ መልስ ጨዋታ በጥሩ ውጤት አሳክተናል።ስለዚህ ጅምራችን ጥሩ ነው የሚባል ነው።አሁንም ይሄንኑ ጥሩ መንፈስ እና ዝግጅት ይዘን ሩዋንዳን ገጥመን ቻን ለመግባት አቅማችን የፈቀደው ሁሉ እናደርጋለን ማለት ነው።ይሄ ብዙ ጫና ውስጥ የሚከተን አደለም ከሁሉም በላይ ተጨዋቾቼ ምንም አንኳን 80 በመቶ ወጣቶችና አዳዲሶች ቢሆኑም አንደ ካፒቴኑ አስቻለው እና ጀማል ጣሰው እነዚህ ሁለቱ ናቸው ሲንየር ሚባሉት እነሱ ጥሩ እገዛ እያደረግሉን በቲሙ ውስጥ ያለው መንፈስ እና ጥንካሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ጫናው እየበለጠ አንዲቀንስ እና ጥሩ ነገር እየጠቀመን ይመስላል።
በተጨማሪ የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ እና አምፐል በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ መሆናቸው አንዲሁም በስታድየሙና በመጫወቻ ሳሩ ደስተኛ መሆናቸው ገልፀዋል።