የጅማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ከክለቡ ጋር ለመለያየት መቃረባቸውን ገለጹ፡፡
አሰልጣኙ ለሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገፅ እንደገለፁት “ለክለቡ ያስገባሁት የመልቀቂያ ደብዳቤ በአመራሮቹ ተቀባይነት አግኝቷል “
“ከክለቡ ጋር ለመለያየት የወሰንኑኩት ለቤተሰቦቼ በቂ ጊዜ ለመስጠት በማሰብ ነው፤ ክለቡን ማሰልጠን ከጀመረኩበት ከዛሬ ሁለት አመት ጀምሮ የተሳካ ስራ መስራት በመቻሌ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
የጅማ ከተማ እግር ኳስ ክለብን ማሰልጠን መነሻ ባደረጉበት የመጀመሪያ ዓመት የከፍተኛ ሊግ ውድድሩን አራተኛ ሆኖ እንደጨረሰ አስታውሰዋል፡፡
በአሁኑ ሰአት ከ ምድብ “ለ” አንደኛ ሆኖ በመምራት ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
የክለቡ ፍላጎት በ2010ዓም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደግ መሆኑን የገለጹት አሰልጣኙ “ከቤተሰብ ተለይቼ የክለቡን ፍላጎት ለማሳከት እንደማልችል በመገንዘቤ ለመልቀቅ ወሰኛለሁ” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
“በማሰልጠን ቆይታዬ የክለቡ ደጋፊዎች የጅማ ከተማ ነዋሪዎችና ተጫዋቾች ከጎኔ በመሆን ያበረታቱኝ በመሆኑ ምስጋናዬ ከፍተኛ ነው” ብለው፡፡
ስለሁኔታው የተጠየቁት የክለቡ አመራሮች መረጃ የሚሰጡት ጉዳዩ ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑን ገልጸዋል።