ኢትዮጵያ መድህን ከወር በፊት ቡድኑን የተረከቡት አሰልጣኝ ደረጄ በላይ ክለቡ ጋር ስላላቸው እቅድ እና ስለ ቀድሞ ቡድናቸው ከሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
ክለቡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 25ተኛ ሳምንት ድረስ ባለው ውጤት በምድብ-ሀ 25 ጨዋታዎችን ተጫውተው በ4የጎል ክፍያ በ31 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያ መድህንን እንዴት አገኘኸው ?
ደረጄ:- ክለቡ ጥሩ ክህሎት ያላቸው ልጆች አሉት በአሁኑ ሰዓት እየሰራሁ ያለሁት ለቀጣይ አመት እሚሆነኝን ቲም እየሰራሁ ነው፡፡ አሁን ያለው ስብስብ በቀድሞ አስልጣኝ ያለውን ቲም ነው የያዝኩት አሁን ያለውን ቲም እንደ አዲስ ለኔ የጨዋታ ታክቲክ በሚሆን መልኩ መገንባት አለብኝ፡፡ ለቀጣዩ አመት ከራሴ ፍልስፍና ጋር እሚሄዱ ተጨዋቾች ለመስፈረም እና ክለብ ውስጥ ምርጥ እሚባሉ ልጆችን ውል ለማደስ እየተነጋገርኩ ነው፡፡
- ማሰታውቂያ -
ደረጄ- ያሉት ነገሮች እንዳሉ ነው፡፡ ከጀመርኩ ቅርብ ግዜ ነው ፡፡ያሉብንን ችግሮች ተቀራርበን ለመፍታት እየሞከርን ነው፡፡በቀጣዩ ዓመት ክለቡን ወደ ኘሪሜየር ሊግ እንደማሳድገው ቃል ገብቼላቸዋለሁ፡፡
ከቀድሞው ክለብህ ጅማ አባቡና ጋር ያለህ ግኑኘነት ምን ይመስላል ፡፡ ክለቡ በኘሪሜየር ሊጉ ላለመውረድ እየታገለ ይገኛል ?
ደረጄ:- ለጅማ ትልቅ አዲስ ነገር ፈጥሬያለሁ ፡፡አሁን ከተማ ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ ጅማ አባቡና የፈጠረው ነው፡፡ ጅማ ከተማ ከተመሠረተ 30ዓመቱ ነው፡፡ ጅማ አባቡናን ከተመሠረተ በ3ዓመቱ ነው ወደ ኘሪሜየር ሊጉ ያስገባነው፡፡ ከክለቡ አመራሮች ጋር መልካም ግንኙነት ነው ያለኝ፡፡ ጅማ አባቡና ባይወርድ መልካም ነው፡፡ የመወረድ ስጋት ውስጥ በመሆኑ እንደኔ እሚጨነቅ ያለ ሰው እሚኖር አይመስለኝም፤ ክለቡ ሲቆይ ነው ያንተም ስም አብሮ ሊቆይ እሚችለው፤ ከወረደ በኃላ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም ወይ ሊቀጥል ወይም ሊፈርስ ይችላል ለራሴ ስም ስል ክለቡ በፕሪሚየር ሊጉ እንዲቆይ እፈልጋለሁ ፡፡