በ11ኛው ሳምንት የኢትዩጲያ ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻን አስተናግዶ 2-1 ካሸነፈ በኋላ
የሀዋሳ ከተማ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ለመገናኛ ብዙሀን ደለለኝ ደቻሳ ደግሞ ለሀትሪክ ስፖርት አስተያየታቸውን ሰተዋል።
ለማንኛውም እግዚያብሔር ይመስገን ባለቀ ደቂቃ ግብ አግብተን አሸንፈን ወጥተናል አዲሴ ካሳ ሀዋሳ ከተማ
ስለጨዋታው
- ማሰታውቂያ -
“በጨዋታው ነጥብ አልጣልንም 90+ ስለሆነ በጣም ከባድ ነበር።በተለይ ከእረፍት በኋላ የኛ አጨዋወት ተቀይሯል ማለት ይቻላል። ምክያቱም ነጥብ ለመያዝ ያደረግነው እንቅስቃሴ ጨና ውስጥ እንደንገባ አድርጎናል። ውጤት የማስጠበቁ ነገር ሁሉም ጋር አንድ እየሆ ነው።ግብ ካገቡብን በኋላ ደግሞ የተሻልን መሆን ችለናል። ግብ ካሰቆጠርን በኋላ እንደመጀመሪያው ብንጫወት የተሻልን ይሆን ነበር እዚህ ደረጃም አንደርስም ነበር። ለማንኛውም እግዚያብሔር ይመስገን ባለቀ ደቂቃ ግብ አግብተን አሸንፈን ወጥተናል”።
በዛሬው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ እድለኛ ነው ብዬ አሰባለሁ
ደለለኝ ደቻሳ የወላይታ ድቻ ጊዜያዊ አሰልጣኝ
ስለጨዋታው
“ጨዋታውን እንዳያችሁት ከጨዋታ ጨዋታ መሻሻሎችን እያመጣን ነው።እኛምበዛ ላይ ባሉን ከፍተቶች ላይ እየሰራንነው ያለነው።በዛሬው ጨዋታ በመጀመሪ 25ደቂቃ ባለሜዳዎቹ ጥሩ ነበሩ የነሳን ጨዋታ በማየት በተወሰነ ደረጃ ሜዳውስጥ ባለው እንቅስቃሴ ሜዳውስጥ ልጆችን ቅርፅ በማስያዝ ሜዳውስጥ የተሻለ ተንቀሳቅሰን እረፍት ወተናል።ከረፍት በኋላ እንደተመለከታችሁት ባለው እንቅስቃሴ እኛ ሙሉ ለሙሉ የተሻልን ነን ብዬ ማምነው።ወላይታ ድቻ ዘንድሮ በሜዳውምከሜዳውም ውጪ ሲጫወት የማጥቃት ስልት ነው እየተከተለ ያለው።በዛሬው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ እድለኛ ነው ብዬ ሰባለው”::