በርካታ ተጨዋቾችን በማስፈረም ላይ ሚገኘው ሰበታ ከተማ የመስመር አማካኙን አስቻለው ግርማን ከጅማ አባጅፋር አስፈርሟል።
ከመስመር በመነሳት በሚያደርጋቸው ፈጣን እንቅስቃሴዎች ሚታወቀው የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን፣የኢትዮጵያ ቡና፣ሃዋሳ ከተማ፣ጅማ አባጅፋር ተጨዋች አስቻለው ግርማ የውበቱ አባተ የክረምቱ 10ኛ ፈራሚ ሆኖ ሰበታ ከተማን መቀላቀል ችሏል።
ሁነኛ የመስመር ተጨዋቾች ሲጠቀም ሚታየው ውበቱ በቀጣይ ቀናት ሌሎች የመስመር አጥቂዎች ወደ ቡድኑ ሊቀላቅል እንደሚችል ይገመታል።