አሸናፊ በቀለ አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተመርጠዋል
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያወጣውን ባለ 7 ነጥብ የቅጥር ማስታወቂያ ተከትሎ ከ20 የበለጡ የሀገር ዉስጥና የባህር ማዶ አሰልጣኞች ያመለከቱ ሲሆን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከቴክኒክ ኮሚቴው የቀረበለትን ሀሳብ በማጽደቅ የአዳማ ከተማው አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በዛሬው እለት መምረጡን አስታውቋል፡፡በአስልጣኙ ቅጥር እና ሌሎች ጉዳየች ፌዴሬሽኑ በዚህ ሳምንት ጋዜጣ መግለጫ እንደሚጠራ አስታውቋል፡፡