ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ በ2009 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የውድድር ተሳትፎ የበላይነት በማጠናቀቅ በዘንድሮው የ2010 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ መቀላቀሉን ተከትሎ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከ14 በላይ የተለያዩ ተጫዋቾች ከፕሪሜየር ሊግ ክለቦችና ከወጪ በማስመጣት ቢያስፈርምም ቡዱኑ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ በ13 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ችሏል።
ወልዋሎ አዲግራት ለተከታታይ ጨዋታ ነጥብ መጣሉ ተከትሎ ። አሰልጣኝ ብርሃነ ገ/እግዚአብሔርን ማሰናበቱ የሚታወስ ነው። ይህንንም ተከትሎ ቦርዱ በ13ኛ ሳምንት ጨዋታ በአዳማ ከተማ 3-0 በተሸነፈበት ማግስት በዲስፕሊንና ከአቅም በታች በመጫወት በሚል ለ8 ያክል ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የተሰጣቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም ቡድኑ ለ3 ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መስጠቱ እሚታወስ ነው።ክለቡ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የተሰጣቸውን ተጫዋቾች ስም ዝርዝር ከመናገር ተቆጥቧል።
ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ በ13 ጨዋታዎች; 7 አቻ በመውጣት በ4 ጨዋታ ተሸንፎ ፤ 2ጨዋታዎችን ብቻ በማሸነፍ በ13 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ችሏል።
በሊጉ የ13 ሳምንት ጉዞ ለተጫዋቾቻቸው ማስጠንቀቂያ ከስጡ ክለቦች መካከል ወላይታ ድቻ ፤ መቐለ ከተማ፤አርባምንጭ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው እሚታወስ ነው።
ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ ከአቅም በታች በመጫወትና በዲስፒሊን ለ8ተጫዋቾች ማስጠንቀቂያ ሰጠ
Managing Editor at Hatricksport Website