የመጀመርያ የፕሪሜየር ሊግ ጨዋታቸውን ለማድረግ በዝግጅት ላይ ሚገኙት ሽረዎች በ2008 ሽረ ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲያድግ ቡድኑ በዋና አሰልጣኝነት በመምራት ከፍተኛ ኣስተዋፅኦ ያበረከተውን የቀድሞው የኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ምድር ባቡር፣ትራንስ ኢትዮጵያ፣ጉና ንግድ ተጨዋች ገብረኪሮስ ኣማረን በቴክኒካል ዳይሬክተርነት ቀጥሯል።
ከተመስረተ በኣጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግን የተቀላቀለው ሽረ እንዳስላሰ የፊታችን እሁድ የመጀመርያ ጨዋታውን ወላይታ ድቻን በማስተናገድ ይጀምራል።