የትግራይ አሰልጣኞች ማህበር ትናንት ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ማህበሩ በይፋ ህጋዊ አውቅና አግኝቶ ወደ ስራ አንደተሰማራ ገልፀዋል።
በተጨማሪ የማህበሩ ሊቀ መንበር አቶ ዳንኤል ተስፋይ ማህበሩ ከተመሰረተ የተወሰኑ ጊዜዎች አንደተቆጠሩ ሆኖም ግን በይፋ ወደ ስራ መግባታችን ለህዝቡ ለሌሎች ሚድያዎች ለማሳወቅ ጋዜጣዊ መግለጫው አንደተዘጋጀ፣ከዚህ በፊት በክልሉ አንደዚህ አይነት ማህበሮች ተመስርተው አንደነበር ሆኖም ግን በብዙ ምክንያቶች የታሰበላቸው ግብ ሳይመቱ አንደፈረሱ ና አሁን የተመሰረተው ማህበር ተመሳሳይ እጣ ፈንታ አንዳይገጥመው ጥናት የተደረገለት ራእይ ይዘው አንደተነሱ ገልጸዋል።በተጨማሪ አቶ ሚኪኤለ የማህበሩ ዋና ራእይ የክልሉና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማሳደግ አንደሆነና፣ለራእዩ መሳካትም አሰልጣኞች ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ ስለሆነ ማህበሩን በማቋቋም በማህበሩ ስር ሚገኙ አሰልጣኞች ዘመኑ የደረሰበት ስልጠና አንዲያገኙ ለማድረግ አንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ማህበሩ በክልሉ ነባር ተጨዋቾች መሪነት አንደተመሰረተና የክልሉ አሰልጣኞች ከኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽን ከክልሉ ሊያገኙት ሚገባ የተሻሻሉ ስልጠናዎች በግዜ አንዲያገኙ ማድረግ አንደሆነና ከጀማሪ አሰልጣኝ አስከ ከፍተኛው ኢንስትራክተር በማህበሩ አንደተመዘገቡ ማህበሩ አንዲመሰረት ከተባበሩት መሃከል የሆኑት የክልሉ የቀድሞው ተጨዋች ሚኪኤለ አምሀ አስታውቀዋል።
- ማሰታውቂያ -
ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የማህበሩ የውደባ ኃላፊ አቶ ግርማይ ምሩጽ ማህበሩ 33 አሰልጣኞች ሆነው አንደመሰረቱት አሁን 66 አባሎች አንዳሉት ገልጸዋል።
በመጨረሻም ማህበሩ እሁድ መስከረም 25 በሚላኖ ሆቴል የማህበሩ አባላትና ተጋባዥ አንግዶች በተገኙበት አንደሚያካሂዱ አስታውቀዋል።