በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ነገ ቅዱስ ጊዮርጊስ የአህጉሪቱን ትልቅ ክለብ በአዲስ አበባ ስታድየም ያስተናግዳል። ቅዱስ ጊዮርጊስ በምድቡ የመጀመርያ ጨዋታዉ ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንቶ የወቅቱን የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ሻምፒዮኑን ማሜሎዲ ሰንዳዉስን ገጥሞ ከሜዳዉ ዉጭ አንድ ነጥብ ይዞ መመለሱ ይታወሳል። የቱኒዝያዉ ክለብ ኢስፔራንስ በአፍሪካ የክለቦች ደረጃ፣ በ1617 ነጥብ በቀዳሚነት የተቀመጠ ክለብ ነዉ።
ክለቡ፣ የቱኒዝያን ሊግ 27 ጊዜ አሸንፏል። የቱኒዝያን ካፕ 15 ጊዜ፣ የቱኒዝያን ሱፐር ካፕ ደግሞ 3 ጊዜ ወስዷል። አሁን እየተወዳደረበት የሚገኘዉ የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ደግሞ በ1994 እና በ2011 2 ጊዜ ወስዷል። በተጨማሪም፣ በ1999፣ 2000፣ 2010 እና 2012 የፍፃሜ ተፋላሚ ነበር። የአፍሪካን ካፕ ዊነርስ ካፕን በ1998 1 ጊዜ ሲያሸንፍ፣ 1987 ላይ ለፍፃሜ ደርሷል። በ1997 ያሸነፈዉን የካፍ ሱፐር ካፕን ጨምሮ ሌሎች ክብሮችንም ያሳካ ክለብ ነዉ።
በቱኒዚያዊው አንጋፋ አሰልጣኝ ፋውዚ ቤንዛርቲ የሚሰለጥነው የኤስፓራንስ ቡድኑ ዛሬ ከሰዓት በአዲስአበባ ስታዲየም የማጥቃት ላይ መሰረት ያደረገ ለምምድ መስራት ችለዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ዋና አሰልጣኙን ማርት ኖይ በህመም ምክኒያት ያጣው ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቡን ለረጅም አመታ በተጫዋችነት እና በአሰልጣኝነት እያገለገሉ ባሉት አሰልጣኞች ፋሲል ተካልኝ እና ዘሪሁን ሸንገታ የሚመራ ይሆናል ፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ
ግምታዊ አሰላለፍ
ግብ ጠባቂ – ሮበርት ኦዶንካራ
ተከላካዮች፡- አበባው ቡጣቆ፣ ደጉ ደበበ፣ ሳላሃዲን በርጌቾ፣
አስቻለው ታመነ
የተከላካይ አማካዮች፡- ናትናኤል ዘለቀ፣ ምንተስኖት አዳነ
የመስመር እና የአጥቂ አማካዮች- ፕሪንስ ሰቬርኒሆ፣ አዳነ ግርማ፣
አብዱልከሪም ኒኪማ
አጥቂ፡- ሳላሃዲን ሰኢድ
ጨዋታውን ማን ይዳኙታል
ቦትስዋናዊው ጆሽዋ ቦንዶ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኤስፔራንስ ደ
ቱኒዝ ጨዋታን በዋና ዳኝነት ይመሩታል፡፡ እኚህ ዳኛ የቅዱስ
ጊዮርጊስን ጨዋታ ሲመሩ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም፡፡
በ2016 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ
ወደ ኮንጎ አቅንቶ ከወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ባለ ክብር ቲፒ
ማዜንቤ ጋር ጨዋታውን ሲያደርግ እኚህ ዳኛ ጨዋታውን በዋና
ዳኝነት መምራታቸው ይታወሳል፡፡ ጆሽ ቦንዶ በወቅቱ የጨዋታ
መጠናቀቂያ ላይ ለባለሜዳው ቲፒ ማዜንቤ የፍጹም ቅጣት ምት
መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ እንዲሁም በጨዋታው ላይ 3
የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ ለእንግዳው ቡድን ቅዱስ ጊዮርጊስ
አሳይተዋል፡፡