ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለመምጣት በመታገል ላይ የሚገኘው መድን ክለብ ከሁለት ሳምንታት በፊት ከአሰልጣኝ ሻምበል መላኩ ጋር በስምምነት መለያየቱ ይታወሳል። የእሳቸው ምትክ ይሆንለት ዘንድ ደረጀ በላይን ከሰሞኑ ቀጥሯል። የቀድሞው የምድር ጦር ዝነኛ ተጨዋች ደረጀ ከዚህ በፊት ሰበታ ከተማን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያሳደገው ሲሆን አምናም በጅማ አባ ቡና ይህንን መድገሙ ይታወሳል፤ ነገር ግን “እየደረሰብኝ ያለው ጫና ለራሴ እና ለቤተሰቦቼ ደህንነት ስጋት ፈጥሮብኛል” በሚል ምክንያት ከክለቡ ጋር መለያየቱ ይታወሳል። አሰልጣኝ ደረጀ ነገ ለንባብ ከምትበቃው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ጋር ልዩ ቆይታ አድርጉዋል። በቀጣይ ሙሉ ቆይታውን እንለቀዋለን።