ካሳዬ ኣራጌን በአዲስ አሰልጣኝነት ለመቅጠር ዝግጅት ላይ ያለው ኢትዮጵያ ቡና ከአምስት ተጨዋቾቹ ጋር ተለያይቷል።
የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን 9ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ ቡና ከሳምሶን ጥላሁን፣ ቶማስ ስምረቱ፣ ወንድይፍራው ጌታሁን፣ ክሪዚስቶም ንታምቢ እንዲሁም ከግብ ጠባቂው ወንድወሰን እሸናፊ ጋር መለያየት ችሏል።
በካሳዬ እራጌ እየተመራ ቡድኑን እንደአዲስ እንደሚሰራ እሚገመተው ኢትዮጵያ ቡና ሐምሌ 26 በሚከፈተው የተጨዋቾች ዝውውር ላይ በንቃት ሊሳተፍ እንደሚችል ይገመታል።