ወደ ክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር ዘግይቶ የገባው ኢትዮጵያ ቡና ወንድሜነህ ደረጄን ከባህርዳር ማስፈረም ችሏል።
በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የባህርዳር ከተማን ጠንካራ የተከላካይ ክፍልን በሚገባ የመራው ወንድሜነህ ደረጄ በክረምቱ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለ አምስተኛ ተጨዋች ሆኗል።
ሃብታሙ ታደሰ፣አለም አንተካሳ(ማርዮ)፣ተክለማርያም ሻንቆ ና ሠይፈ ዛኪር ማስፈረም የቻለው ቡና ወንድይፍራው ጌታሁን እና ቶማስ ስምረቱን ያጣውን የተከላካይ ክፍሉን ለማጠናከር ወንድሜነህ ደረጄን ምርጫው አድርጓል።