በሁለተኛ ቀን ውሎ ኢትዮጵያ ቡና የምስራቅ ክልል ተወካዩን ድሬዳዋ ከተማን በአዲስአበባ ስታዲየም 2-1 በሆነ ውጤት በመርታት የሊጉን ጅማሬ በድል ጀምሯል።
በአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ ድል ካደረገው ቡድን ቶማስ ስምረቱና ሱልይማን ሉኩዋ ፋንታ ሚኪያስ መኮንን እና ተመስገን ካስትሮን ወደ ሜዳ ይዘው ገብተዋል።በአንፃሩ ድሬዎች በትግራይ ዋንጫ ያልተጠቀሙባቸውን ግብ ጠባቂው ሳምሶን አሰፋንና አንተህ ተስፋዬን ተጠቅመዋል።
በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ጥሩ መንቀሳቀስ የቻሉት ኢትዮጵያ ቡናዎች በ31ኛ ደቂቃ ላይ ሳምሶን ጥላሁን ላይ የተሰራውን ጥፋት ተክተሎ የእለቱ አርቢትር አማኑኤል የሰጡት ፍፁም ቅጣት ምት እራሱ ሳምሶን አስቆጥሮ 1-0 መምራት አስችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ከግቧ መቆጠር በኃላ ጨዋታው ተጠናቆ በባከነ ሰዓት ኢታሙና ኬይሙኒ ከመስመር በቀጥታ የመታት ኳስ ግብ ተቆጥራ ጨዋታው 1-1 በሆነ ውጤት ወደ መልበሻ ማምራት ችሏል።
በሁለተኛው አጋማሽ ኢትዮጵያ ቡናዎች ሙሉ ሶስት ነጥብ ለማግኘት በሙሉ ሀይል ወደ ጨዋታ መመለስ ችለዋል። ተደጋጋሚ ጨና ፈጥረው መጫወት የቻሉት ቡናዎች ተካለኝ ደጀኔ ያሻማውን ኳስ አሕመድ ረሺድ ሞክሯት የተመለሰችውን ኳስ አቡበከር ናስር ወደ ግብነት ቀይሮ ኢትዮጵያ ቡና ሊጉን በድል የሚጀምርበትን እድል አመቻችቷል።ጨዋታውም በኢትዮጵያ ቡና 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።