የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ዙር ጨዋታ መርኃ ግብር በአንድ ሳምንት እንዲራዘም ተወሰነ።የፕሮግራሙ መራዘም የተገለጸው ዛሬ የሊጉ ክለቦች የአንደኛ ዙር የውድድር አፈጻጸም ሲገመገም ነው።
ለመርሀ- ግብሩ መራዘም እንደ ምክንያትነት የቀረበው ክለቦች ለእረፍትና ለሁለተኛው ዙር የውድድር ዝግጅት በቂ ጊዜ አላገኘንም በማለታቸው መሆኑ ተገልጿል።
ውድድሩ መጋቢት 8 እና 9 እንደሚጀመር ቀደም ብሎ ቢገለጽም በተደረገው የቀን ለውጥ ጨዋታዎቹ መጋቢት 15 እና 16 ቀን 2010 ዓ.ም እንዲካሄዱ ነው ፌዴሬሽኑ የወሰነው።
በመጨረሻም የእጣ ማውጣት ስነ ስረዓት ተከናውኗል።
ሀዋሳ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና
- ማሰታውቂያ -
ፋሲል ከተማ ከአዳማ ከተማ
ኢትዮጵያ ቡና ከ ወልዲያ
ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከ መቐለ ከተማ
መከላከያ ከ ድሬደዋ ከተማ
ወልዋሎ አዲግራት ከ አርባምንጭ ከተማ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወላይታ ድቻ
*ስማቸው በቅድሚያ የተፃፉት ክለቦች በሜዳቸው ይጫወታሉ
ግምገማውን በተመለከተ ከሰዓታት በኃላ በድህረ-ገፃችን መረጃውን እምናቀርብ ይሆናል።