_________________________________
በ2018 ሩስያ ዓለም ዋንጫ ኣፍሪካን በመወከል የተሳተፈው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው የ2019 ኣፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በመሃል ዳኝነት ከሌላኛው ኢትዮጵያዊ ተመስገን ሳሙኤል እና ሱዳንያዊው መሃመድ ኢብራሂም በመጣመር ሚመራ ይሆናል።
በ2009 ኣ.ኣ በፊፋ ስር ካሉት ዳኞች ዝርዝር ውስጥ የተካተተው ባምላክ በ2010 የሴካፋ የፍፃሜ ጨዋታን መምራት ችልዋል።በተለያዩ የኣፍሪካ ዋንጫ ማጣርያዎች እና ውድድሮች እንዲሁም የዓለም ዋንጫ ማጣርያዎችን መምራት የቻለው ባምላክ ዘመናዊ የሆኑ ለዳኝነት ኣጋዥ የሆኑ መሳሪያዎችን በግሉ በማስገባት ኢትዮጵያ ውስጥ ሚታዩትን የዳኝነት ስህተቶችን ለመቅረፍ እየተጋ ይገኛል።