ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የኣፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ እንዲመራ ተመረጠ
ባለፈው ቅዳሜ ግብፅ ካይሮ ላይ በቱኒዝያው ኤስፔሪያንስ ዳቱኒዝ እና እልእህሊ መካከል የተደረገው የኣፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጀመርያ ጨዋታ በግብፁ ክለብ እልእህሊ 3ለ1 አሸናፊነት መጠናቀቁ ሚታወስ ነው፤አወዛጋቢ ውሳኔዎች የታዩበት የሁለቱ ሰሜን እፍሪካ ክለቦች ጨዋታ የመልስ ጨዋታውን የፊታችን ዓርብ በቱኒዝ የሚካሄድ ሲሆን ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በመሃል ዳኝነት ሚመራው ይሆናል።