በኢትዮጵያ ሁለተኛ ዓመቱን እያሳለፈ ሚገኘው ኒኪማ ሁለተኛ የሊግ ዋንጫውን ለማንሳት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።አምና ጊዮርጊስን የተቀላቀለው ኒኪማ ክለቡ ኣምና በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ምድብ ድልድል ውስጥ እንዲገባ ከፍተኛ ሚናን ተወጥቷል።ከ ማሚሎ ዶሰንዳውንስ፣ቪታ እና ኤስፔራንስ ጋር ተመድቦ የነበረው ጊዮርጊስ ምድቡን ኣራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅዋል።ቡሩኪናፋሶዊው ኣማካይ በዘንድሮ ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ በአሰልጣኝ ቫሳ ፒንቶ ከፍተኛ እምነት ከተጣለባቸዉ ተጨዋቾች ኣንዱ ነው።በመጀመርያው ዙር በ4-3-3 ኣሰላለፍ በመሃል ሜዳ ከሚሰለፋ ሦስት ተጨዋቾች ወደ ግራ ኣመዝኖ ሲጫወት የነበረው ኒኪማ በሁለተኛው ዙር ቫስ ፒንቶ የጨዋታቸውን ስልት ወደ 4-2-3-1 በመቀየራቸው ኒኪማ ከኣጥቂ ጀርባ በመጫወት ላይ ይገኛል። በአሰልጣኝ ፒንቶ ነፃ ሚና ተሰጥቶት ሚጫወተው ኒኪማ ጥሩ ሚባል የውድድር ዓመት እያሳለፈ ይገኛል።
ሃትሪክ ስፓርት በዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ውድድር ኣስመልክተን ከኣብዱልከሪም ኒኪማ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በዚህ መልኩ ኣቅርበንላችኃል።
ሃትሪክ፡ በመጀመርያ ለቃለ መጠይቅ ፍቃደኛ ስለሆንክ ኣመሰግናለው።
ኒኪማ፡ ለቃለ-መጠይቅ ስለጋበዝከኝ እኔም ኣመሰግናለው።
- ማሰታውቂያ -
ሃትሪክ: የዘንድሮ ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ፋክክር እንዴት ኣየሀው?
ኒኪማ፡ የዘንድሮ ዓመት ፕሪሜርሊግ በጣም ፋክክር ያለው በጠንካራ ክለቦች የታጀበ ነው።እንዲህ መሆኑ ጥሩ ነው ምክንያቱም ብዙ ክለቦች እንዲያሻሽሉ ኣግዝዋቸዋል፤ፋክክር ሲኖር መሻሻል ይኖራል ተጨዋቾችም የግል ብቃታቸውን እንዲያሻሽሉ ያግዛቸዋል።
ሃትሪክ: የኣሁኑ ዓመት የጊዮርጊስ ኣቋም እንዴት ኣየሀው?
ኒኪማ: ለኔ ከኣምናው በተሻለ ጠንካሮች ነን።በመጀመርያው ዙር ትንሽ ተቸግረን ነበር፤በሁለተኛው ዙር ግን መሻሻሎችን እያሳየን እንገኛለን።
ሃትሪክ፡ በሁለተኛው ዙር ላሳያቹት ለውጥ ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል?በአንደኛው ዙር ለታዩት ችግሮችስ ምክንያት ናቸው ምትላቸው?
ኒኪማ፡ እንደምታቀው ዘንድሮ ብዙ ቅያሬዎችን ኣድርገን ነው የመጣነው።ኣዲስ ኣሰልጣኝ፣ኣዲስ ተጨዋቾች ከማምጣታችን ኣንፃር ለመተዋወቅ ግዜ ኣስፈልጎን ነበር።ኣሁን በሁለተኛው ዙር ብዙ መሻሻሎችን እያሳየን ነው፤ኣሰልጣኙ ከኛ የሚፈልገውን ተረድተን ሜዳ ላይ እያሳያን እንገኛለን እኛ ተጨዋቾችም ሜዳ ላይ በደምብ እየተግባባን ነው።
ሃትሪክ፡ የቫዝ ፒንቶ ኣጨዋወት ዘይቤ እንዴት ኣየሀው?እየተጫወትክበት ያለ ቦታስ?
ኒኪማ፡ ፒንቶ በጣም ጥሩ ኣሰልጣኝ ነው፤ታክቲሽያን ነው ሁሉም ነገሮችን በጥልቀት ይመለከታል ከእሱ ጋር ብዙ ነገሮችን እየተማርኩ ነው።እየተጫወትኩበት ያለው ቦታ በጣም እወደዋለሁ ምክንያቱም ነፃነት ኣለኝ ወደ ፈለግኩት ቦታ በመንቀሳቀስ ነው ምጫወተው።ከተከላካዮች ኳስ መቀበልና ኳስን ከኃላ ማስጀመር እወዳለሁ ለዛም ይመስለኛል ኣስልጣኙ ነፃ ሚና ተሰጥቶኝ እንድጫወት የፈቀደልኝ።
ሃትሪክ፡ ዘንድሮ ከተጫወትካቸው ጨዋታዎች ላንተ ከባድ ጨዋታ የትኛው ነበር?
ኒኪማ፡ ከመቐለ ከተማ ጋር በሁለተኛው ዙር ላይ ያደረግነው ጨዋታ ከባድ ነበር።ለኔ ጨዋታው በዚህ ዓመት እስካሁን ከተደረጉ ጨዋታዎች ምርጡ ጨዋታ ነው።የማጥቃት እንቅስቃሴያችን በደምብ ተቆጣጥረዉት ነበር።ኣንድ የጎል ዕድል ኣገኙ ኣስቆጠሩ እኛም በፍጥነት ነበር መልስ የሰጠነው፤ሦስት ነጥቡን ለማግኘት ተቃርበው ነበር።
ሃትሪክ፡ ከካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በጊዜ መሰናበታችሁ ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል?
ኒኪማ፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ለኛ ጥሩ ጊዜ ኣልነበረም፤በሊጉም ጥሩ ኣልነበርንም እናም የራስ መተማመናችን ኣጥተን ነበር።
ሃትሪክ፡ በዘንድሮ ዓመት ፕሪሜርሊግ የተመቸህ ቡድን?
ኒኪማ፡ ለኔ ጅማ አባጅፋርና መቐለ ከተማ ምርጥ ብቃት እያሳዩ ናቸው ምክንያቱ ከታችኛው ሊግ መጥተው በዚህ ደረጃ መገኘታቸው ቀላል ኣይደለም።
ሃትሪክ: በቅዱስ ጊዮርጊስ ማልያ ካስቆጠርካቸው ጎሎች ላንተ ምርጥዋ?
ኒኪማ፡ በመጀመርያው ዙር ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ላይ ያስቆጠርክዋት ለኔ ምርጥዋ ነች።
ሃትሪክ፡ በስታድየሞች አየታዩ ያሉ የስፓርታዊ ጨዋነት ጉድለት ላይ ምትለው ነገር ካለህ እና ከጊዮርጊስ ደጋፊዎች ውጭ የተመቹህ ደጋፊዎች?
ኒኪማ፡ ስቴድየም ላይ ረብሻ ማየት ያሳዝናል፤እግር ኳስ ሊያቀራርበን እንጂ ሊለያየን ኣይገባም።መቐለ ደጋፊዎች ምርጥ ናቸው፤ ምርጥ ኣቀባበል ኣርገው ነው የተቀበሉን።
ሃትሪክ፡ ኣመሰግናለሁ ኒኪ
ኒኪማ፡ እኔም ኣመሰግናለሁ
ሊጠናቀቅ ሦስት ጨዋታዎች በቀሩት የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ኣምስት ቡድኖች ለዋንጫ በመፎካከር ላይ ይገኛሉ።ኒኪማም ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዋንጫ የማብቃት ሃላፊነት ተጥሎበታል።