በ2009 ዓ/ም ከተስፋ ቡድን ያደገው ተጨዋቾች ሄኖክ አወቀ በፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ እስከ ሰኔ 2010
ዓ/ም ከክለቡ ጋር የሚያቆየው ውል ቢኖርም ከክለቡ ጋር በስምምነት ውሉን በማቋረጥ ተለያይቷል፡፡
ሄኖክ አወቀ ከክለቡ ጋር በተደጋጋሚ በደሞዝ ጭማሪና በውል ማደስ ዙሪያ በተደጋጋሚ ከክለቡ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ለረዥም ጊዜ የቆየ ድርድር በማድረግ ክለቡ ለወደፊት ይጠቅመኛል በማለት ለ2 አመት በሚያቆይ ውል 1.2 ሚሊየን ብር ቢያቀርብለትም ተጨዋቹ ባለመስማማቱ የመልቀቂያ ጥያቄውን ለክለቡ በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።
የሄኖክ አወቀን የልቀቁኝ ደብዳቤ የተመለከቱት የክለቡ ስራ አስፈፃሚዎችና የክለቡ አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ ተጨዋቹ በክለቡ መቆየት የማይፈልግ ከሆነ በጠየቀው መሰረት በስምምነት ውላቸውን በማቋረጥ ተለያይተዋል፡፡
የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብም ያለበትን የተጫዋቾች ክፍተት ለመሙላት ፊቱን ወደ ታዳጊዎች በማዞር በአማራ ሊግ በመወዳደር ላይ ከሚገኘው የክለቡ ተስፋ ቡድን ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴ ያሳዩትን 3 ተጨዋቾች ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል፡፡
አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡ በቀጣይ ቡድናቸውን ለማጠናከር ሁነኛ ካሏቸው ተስፈኛ ታዳጊዬች የመሀል ተከላካይ ዳንኤል ዘመዴ፡የአጥቂ አማካኝ ናትናኤል ወርቁንና፡ በአጥቂ ቦታ ያሬድ አበበን ወደ ዋናው ቡድን ሲያሳድጉ በቀጣይም ተጨዋቾችን ከውጭ ሀገር ከማስመጣት ይልቅ ታዳጊዬች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡