ወላይታ ዲቻ የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ የወንዶች ጥሎ ማለፍ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።
መከላከያ ከ ወላይታ ድቻ በአዲስአበባ እስታዲየም በጥሎ ማለፍ ፍፃሜ ሲያገናኝ በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት ወላይታ ድቻ አሸናፊ ሇኗል
ሁለቱ ቡድኖች ባደረጉት የፍጻሜ ጨዋታ መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
- ማሰታውቂያ -
መከላከያ የወላይታ ዲቻው ተከላካይ ሙባሪክ ሽኩር በ21 ኛው ደቂቃ በራሱ ግብ ላይ ባስቆጠራት ጎል የመጀመሪያውን አጋማሽ 1 ለ 0 እየመራ መውጣት ችሏል።
ከእረፍት መልስ ውጤቱን ለመቀልበስ ወደ ሜዳ የገቡት ወላይታ ድቻዎች በአላዛር ፋሲካ የፍጹም ቅጣት ምት ጎል አቻ መሆን ችለዋል።
ከዚህ በኋላ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
አሸናፊውን ለመለየትም ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል።
አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት በመለያየታቸው በተሰጠው የፍጹም ቅጣት ምት ለወላይታ ድቻ ተክሉ ታፈሰ፣ አብዱልሰመድ አሊ ፣አላዛር ፋሲካ፣ ወንድወሰን ገረመው ሲያስቆጥሩ በእለቱ ጨዋታ ድንቅ የነበረው ፈቱዲን ጀማል ፍጹም ቕጣት ምት አምክኖአል
ለመከላከያ ባዬ ገዛኸኝ እና ሳሙኤል ሳሊሶ ሲያስቆጥሩ አወል አብደላ ይድነቃቸው ኪዳኔ በመሳታቸው ወላይታ ድቻ 4 ለ 2 አሸንፏል ፡፡
ወላይታ ዲቻ በቀጣዩ አመት ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ መሆኑንም አረጋግጧል።