በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በወላይታ ሶዶ ሁለ ገብ ስታዲየም ወላይታ ዲቻ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1-0 አሸንፏል ።
ጎሏን በ36ኛው ደቂቃ ላይ ከማዕዘን የተሻገረለትን ኳስ ወደ መሬት በማውረድ ያስቆጠረው ሰባት ቁጥሩ አናጋዉ ባደገ ነው።
በመጀመሪያዉ የጨዋታ አጋማሽ ወላይታ ዲቻዎች ኳስ በማደራጀት የተሻሉ ሲሆኑ ያገኟቸውን ዕድሎች ቢያስቆጥሩ ኖሮ የጎል ልዩነቱ ከዚህም ሊሰፋ ይችል ነበር።
- ማሰታውቂያ -
በተለይ በመጀመሪያዎቹ 20 ደቂቃዎች የኤሌክትሪክ በረኛ ስራ የበዛበት ሲሆን በ9ኛዉና 17ኛዉ ደቂቃ ላይ 23 ቁጥሩ ጸጋዬ ብርሃኑና 13 ቁጥሩ ዳግም በቀለ የሳቷቸዉ ኳሶች ደጋፊዎችን ያስቆጩ ነበሩ።
ኤሌክትሪክ በመከላከልና መልሶ በማጥቃት ወደ ጨዋታው ለመመለስ ቢሞክርም የተሻሉ የጎል ዕድሎችን ሳይፈጥር ቀርቷል።
የአስልጣኞች አስተያየት
የወላይታ ዲቻ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ “ተጋጣሚያችንን ተጭነንና አጥቅተን በመጫወት ሙሉ ነጥብ ይዘን ለመውጣት ነበር የተዘጋጀነው ተሳክቶልናል” ብለዋል።
“ጎል ለማስቆጠር ካለን ጉጉት የተነሳ ያገኘናቸውን አጋጣሚዎች እንዳንጠቀም ተጽዕኖ ፈጥሮብናል” ያሉት አሰልጣኙ ቀሪ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ስጋት ለመውጣት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
የኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰልጣኝ ብርሃኑ ባዩ “ወላይታ ዲቻ ረጃጅም ኳስ በመጫወት የሚያስቸግር ቡድን በመሆኑ ተከላክለን ነጥብ ለመያዝ ነበር አልተሳካልንም” ብለዋል
“በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ የተገኘውን አጋጣሚ ወደ ጎል መቀየር ያለመቻላችንና ሜዳው ለጨዋታ አመቺ ያለመሆኑ ዋጋ አስከፍሎናል” ብለዋል።
መልካም የሆነ የዳኝነት ሥነ-ሥርዓት ማየታቸውን ገልጸው የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች የድጋፍ አሰጣጥ ለኳስ ዕድገት ተስፋ የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል።
የደረጃ ሰንጠረዥ
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
---|---|---|---|---|
1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ | 24 | 22 | 46 |
2 | ሲዳማ ቡና | 26 | 9 | 46 |
3 | ደደቢት | 26 | 15 | 45 |
4 | ኢትዮጵያ ቡና | 26 | 11 | 43 |
5 | አዳማ ከተማ | 26 | 8 | 43 |
6 | ፋሲል ከተማ | 24 | -1 | 35 |
7 | መከላከያ | 26 | -9 | 32 |
8 | ሀዋሳ ከተማ | 25 | 1 | 31 |
9 | አርባምንጭ ከተማ | 25 | -2 | 31 |
10 | ወልዲያ ከተማ | 25 | -2 | 30 |
11 | ወላይታ ድቻ | 26 | -10 | 29 |
12 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ | 26 | -2 | 28 |
13 | ጅማ አባቡና | 26 | -4 | 28 |
14 | ድሬዳዋ ከተማ |
25 | -7 | 28 |
15 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ |
25 | -13 | 24 |
16 | አዲስ አበባ ከተማ | 26 | -16 | 19 |