ከአሸናፊ በቀለ ጋር የተለያዩት ወላይታ ድቻዎች በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከደቡብ ፖሊስ ጋር ያሳለፈውን ገብረክርስቶስ ቢራራን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥሯል።
በ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላለመውረድ የተጫወተው ወላይታ ድቻ በቀጣይ ዓመት ውድድር በገብረክርስቶስ ቢራራ እየተመራ ብርቱ ተፎካካሪ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
የኳስ ቁጥጥር ላይ መሰረት ያደረግ አጨዋወትን ሚከተሉት ገብረክርስቶስ ቢራራ ለእጨዋወታቸው ሚመቹ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ሐምሌ 25 በተከፈተው የተጨዋቾች ዝውውር ላይ በንቃት እንደሚሳተፉ ይገመታል።