ባህር ዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን
ስላሸነፈበት የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ የመጀመሪያ
ጨዋታ
“ወልቂጤ ከተማን ያሸነፍንበት የሲቲ
ካፕ የመክፈቻ ጨዋታ ለእኛ ብዙ አስደሳች
ባይሆንልንም አሁን ላይ ካለን አቋም አንፃር
ግን የበለጠ ጠንክረን መስራት እንዳለብን
ያመላከተን ነው፤ ስለዚህም በድክመታችን
ላይ ከፍተኛ ትኩረት አድርገን በመምጣት
በቀጣይነት ጥሩ ቡድንን እንገነባለን”፡፡
ስለነበራቸው ጠንካራ እና ደካማ ጎን
“ባህርዳር ከተማ ድል ባደረገበት
የመጀመሪያው ጨዋታ የነበረው ጠንካራ ጎን
አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ኳስ የሚጫወት ጥሩ
ቡድንን ለመስራት ያደረገው ጥረት ነው፤
በእዚህ አጨዋወት ውስጥም ኳስ እግራችን
ላይ ለማቆየት እንጥርና ወዲያው ወደ
መልሶ ማጥቃት አጨዋወት ውስጥም እንገባ
ነበርና ይሄን የፕሪምየር ሊግ የውድድር
ተሳትፎአችን ውስጥ ስንገባ የበለጠ አስቀጥለን
እንጓዝበታለን፤ የቅዳሜው ጨዋታ ላይ
በደካማ ጎንነት የምጠቅሰው ደግሞ የቡድናችን
አጨዋወት ይቆራረጥ እና ለተጋጣሚያችንም
ወልቂጤ ከተማዎች በነፃነት እንዲጫወቱ
ክፍተት /ስፔስ/ ቦታ እንሰጣቸው ነበርና
ለቀጣይ ጨዋታዎች ግን እዚህ ላይ ያሉብንን
ድክመቶች አስተካክለን የምንመጣበት
ይሆናል”፡፡
ስለ ተጋጣሚያቸው ወልቂጤ ከተማ
“ወልቂጤ ከተማ ከታችኛው ሊግ የመጣ
በመሆኑና ከእንዲህ ያሉም ክለቦች ጋር
ስትጫወት ደግሞ ለግጥሚያው አንድ
ነገር ለመስራት በጣም ተነሳስተው /ሞቲቬት/
ሆነው ስለሚመጡብህ እኛን ፈትነውንም
ነበር”፡፡
የጨዋታው አሸናፊ መሆናቸው ይገባቸው
ስለመሆኑ
“አዎን፤ አሸናፊ መሆናችን ይገባናል፤
እንደውም ያገኘናቸውን የጎል እድሎች
ከአጨራረስ ችግር ጋር በተያያዘ ወደ ጎልነት
መቀየር አቃተን እንጂ ከአንድ ጎል በላይም
ማስቆጠር ነበረብን”፡፡
የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ የጨዋታው ኮከብ
/ማን ኦፍ ዘ ማች/ ተብሎ ስለመሸለሙ
“የቅዳሜው ጨዋታ ላይ አንድ ተጨዋች
ብቻ መሸለም ስላለበት የግጥሚያው ኮከብ
ተብዬ ብሸለምም ለእኔ ግን የጨዋታው ኮከብ
የነበረው ቡድናችን ነበር”፡፡
አዲስ ክለቡ ከሆነው ባህርዳር ከተማ ጋር
በእዚህ ዓመት በምን መልኩ እንደሚጓዝ
“የእግር ኳስ ተጨዋችነት ጉዞዬን
በተመለከተ ከእዚህ በፊት በተደጋጋሚ
እንደነገርኩህ በራሴ አመለካከት ከዓመት
ወደ ዓመት በመሻሻል ላይ የሚገኝ ነው፤
አሁን ባለሁበት አዲሱ ክለቤ ውስጥ ደግሞ
የቡድኑም ሆነ የአሰልጣኛችን ፋሲል
አጨዋወት እንደዚሁም ደግሞ የባህር ዳር
ስታዲየም ሜዳም ሰፋ ያለ መሆኑ እኔ
ለምፈልገው አጨዋወቶች አሁን የገለፅኳቸው
ምክንያቶች ምቹዎች ስለሆኑም ዘንድሮ
ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ለክለቤ ጥሩ ነገርን
በመስራት የውድድር ዓመቱን በመልካም
እና በስኬታማነት ብቃቴ አጠናቅቃለው ብዬ
አስባለው”፡፡