ወልዋሎ አዲግራት አራት ተጨዋቾችን አስፈረመ
በዮሐንስ ሳህሌ እየተመራ ቡድኑን እንደ አዲስ እያዋቀረ እሚገኘው ወልዋሎ አዲግራት የአራት ተጨዋቾችን ፊርማ ማጠናቀቅ ችሏል።
በጉዳት ምክንያት ለአንድ ዓመት ያህል ከሜዳ እርቆ የቆየው አይናለም ሃይሉ ቢጫ ለባሾቹን መቀላቀል ችሏል።ደስታ ደሙና በረከት ተሰማን ያጣው ወልዋሎ አይናለምን ማስፈረሙ ተከትሎ ሁለቱ ተጨዋቾች ትተውት እሚሄዱትን ክፍተት ለመድፈን ሊረዳቸው እንደሚችል ይገመታል።በ2013 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ ባረገው ጉዞ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተው የቀድሞው የመከላከያ፣ደደቢት ና ፋሲል ከነማ ተጨዋች አይናለም ሃይሉ ወልዋሎን መቀላቀሉ ተከትሎ ከቀድሞ አሰልጣኙ ዮሐንስ ሳህሌ ጋር በድጋሚ እሚገናኝ ይሆናል።
በተጨማሪ ወልዋሎ ሁለት ናሚቢያውያን አጥቂዎች ማስፈረም ችሏል።አንደኛው ባሳለፍነው የውድድር ዓመት የድሬዳዋን አጥቂ ክፍል የመራው ኢታሙናይ ኬይሙኒ ሲሆን ሁለተኛው ደሞ ጆናስ ሎሎ ይባላል።
- ማሰታውቂያ -
መሃል ክፍል ላይ አፍወርቅ ሃይሉ፣አማኑኤል ጎበና ና ብርሃኑ አሻሞን ያጣው ወልዋሎ ጋናዊው ኬኔዲ አሽያን ከኢራቁ ክለብ ዳርባዲንክሃን ማስፈረም ችሏል።
በ2010 ለሲዳማ ቡና ፈርሞ ያልተሳካ ጊዜ ያሳለፈው ኬኔዲ በ2013 የእፍሪካ ዋንጫ ከ20 ዓመት በታች እንዲሁም ዓለም ከ20 ዓመት በታች ውድድር ሃገሩ ጋናን ወክሎ መጫወት ችሏል።