በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ተስተካካይ መርሃ ግብር ሽሬ ላይ ወልዋሎ አዲግራት ከ መቐለ ከተማ ሰኞ 9 ሰዓት ሊደረገ ኘሮግራም ወጦለት የነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከፀጥታ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የክልሉ ኮማንድ ፖስቱ ማገዱን ተክቶሎ ጨዋታው እንዳልተካሄደ እሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድርና ስነስርዓት የቀንና ቦታ ለውጥ በማድረግ ኘሮግራሙን የፊታችን ዓርብ ግንቦት 17 ቀን 2010 ቀሪ 45 ደቂቃ በአዲስአበባ ስታዲየም እንደሚካሄድ አሰታውቋል።
በሊጉ 17ኛ ሳምንት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት መቐለ ከተማን በአሳሪ አልማሀዲ የመጀመሪያ አጋማሽ በተቆጠረች ግብ እየመራ ጨዋታው በደጋፊዎቻቸው ረብሻ መቋረጡ እሚታወስ ነው።