በክረምት የተጨዋቾች ዝውውር ደደቢትን በመልቀቅ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን የተቀላቀለው አስራት መገርሳ ከግማሽ አመት ቆይታ በኃላ ክለቡን ተሰናብቷል።
እሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን በእሰልጣኝነት ከቀጠረ በኃላ መሻሻሎችን እያሳየ ያለው ወልዋሎ ከቀድሞው የደደቢት፣ዳሽን ቢራ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ የመሐል አማካይ በተጨማሪ ከ ዋለልኝ ገብሬና ዮሐንስ ሽኩሩ ጋር መለያየታቸው የሚታወስ ነው።
በግማሽ ዓመት የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ክርስቶፈር ችዞባን ብቻ ያስፈረሙት ቢጫ ለባሾቹ በሚቀጥሉት ቀናት አዲስ ተጨዋች ሊያስፈርሙ እንደሚችሉ ይገመታል።