በቅርቡ የአንድ ዓመት ቆይታ ያረገበትን ሶምሃን በስምምነት የለቀቀው ዑመድ በቅርቡ ወደ ሚጀምረው የግብፅ ፕሪምየር ሊግ የተቀላቀለውን አስዋንን ተቀላቅሏል።
በግብፅ በቆየባቸው 4 ዓመታት ለኣራት የተለያዩ ክለቦች የተጫወተው ዑመድ ኡኩሪ በአምስተኛ አመት ቆይታው ለአስዋን ለመጫወት ተስማምቷል።
ኢኤንፒፒአይ፣አልኢትሃድ አሌክሳንድርያ፣ኤልኢንታግ ኤልሃረቢ እና ሶምሃ ዑመድ ከዚህ ቀደም የተጫወተባቸው ክለቦች ናቸው።