የሎዛ አበራ ግብ አግቢነት ማንም ተከላካይ ሊያቆመው አልቻለም አሁንም ማምረቷን ቀጥላበታለች
ሎዛ አበራ ትላንትም ለክለቧ ሁለት ግቦችን አስቆጥራለች።
ትላንት ምሽት በማልታ ሊግ ቢርኪርካራ ከሜዳው ውጭ በቻርለስ አቤላ ስታዴም ስዌኪ ዩናይትድን ገጥሞ 5-0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ። ኢትዮጵያዊቷ ሎዛ አበራ በ 65ኛው ደቂቃ እና 80ኛው ደቂቃ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችላለች። በጀመሪያው ዙር 4-1 አሸንፈው የነበሩት ቢሪካርካራዎች ሎዛ አበራ አንድ ግብ ማስቆጠሯ አይዘነጋም ትላንት ደግሞ ሁለት ግቦችን አክላ በከስዌኪ ዩናይትድ መረብ ላይ ያሳረፈችው ግብ ወደ ሶስት ከፍ አድርጋለች፡፡ በዚህ ውጤት መሰረት ቢርኪርካራ ከስዌኪ ዩናይትድን የነበረውን የነጥብ ልዩነት ወደ 6 ከፍ ማድረግ ሲችሉ። ሎዛም በማልታ ሊግ ያስቆጠረችው ግብ 23 ማድረስ ችላለች። በወዳጅንት 1 ግብ ብሎም በሱፐር ካፕ ደግሞ 3 ግቦችን በማስቆጠር ሎዛ ወደ ማልታ አቅንታ ያስቆጠሰቻቸው አጠቃላይ ጎሎች 27 አድርሳለች። ይህ ማለት ደግሞ ሎዛ በተሰለፈችበት ጨዋታ ቱሉ ግብ ሳታስቆጥር የወጣችበት ጨዋታ የለም።