ሀትሪክ፡- የልጅነት ህልምህን እየኖርክ
ነው ወይስ?
ሙጂብ፡- ህልሜ ላይ እየኖርኩ ነው፡፡
መሆን የምሻው እግር ኳስ ተጨዋች መሆን
ነበር፡፡ ትምህርቴን እያቋረጥኩ ነበር ኳስ
ስጫወት የነበረውና…. ህልሜ ላይ ፍላጎቴ
ላይ እየኖርኩ ነው ማለት እችላለው፡፡
ሀትሪክ፡- በክለብ ደረጃ የት የት
ተጫወትክ?
ሙጂብ፡- የኳስ ህይወቴ የጀመረው
በሲዳማ ቡና ነው…. ከዚያ ውጪ
የተጫወትኩባቸው ክለቦች ሀዋሳ ከተማ፣
አዳማ ከተማና ፋሲል ከነማ ናቸው፡፡
ሀትሪክ፡- ለአንተ የህይወት ጉዞ ስኬት
ወይም አሁን ለደረስክበት ደረጃ እንድትደርስ
አድርጓል የምትለው ባለውለታ አሰልጣኝ
ማነው?
ሙጂብ፡- ትልቅ ምስጋናዬን የማቀርብ
ለትና የማመሰግነው የሲዳማ ቡናው ዋና
ስራ አስኪያጅ መንግሥቱ ሳሳሞ ነው፡
፡ ከርሱ ውጪ በወቅቱ አሰልጣኝ የነበረው
ታረቀኝ ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ ከወረዳ
ውድድር ላይ አግኝተው አስፈርመው
በህልሜ ላይ እንድኖር አድርገውኛልና ከልብ
አመሰግናቸዋለው፡፡
ሀትሪክ፡- በኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ፉክክር
ላይ ነህ በ29ኛው ሳምንት ደግሞ ፎርፌ
አግኝታችኋል በዚህም 3 ግብ ለክለባችሁ
ተሰጥቷል ግቦቹ ለኔ በሆኑ ወይም በስሜ
በተመዘገበ አላልክም?
ሙጂብ፡- (ሳቅ በሳቅ) አዎ
ብያለው፡፡ በጣም ሳስበው ሁሉ
ነበር… ሆኖም ግን ዋናው ነጥቡ
ለክለቡ የሚያስፈልግ በመሆኑ
ባገኘነው 3 ግብም ተደስቻለሁ
በርግጥ ብንጫወት ደስ ይለኝ
ነበር ነገር ግን አጋጣሚው ለኛ
ጥሩ በመሆኑ አልተከፋሁም፡፡
ሀትሪክ፡- በዘንድሮው 29
ጨዋታ ነጥብ በመጣላችሁ
የተከፋህበት.. ስላሸነፋችሁ
ደግሞ የተደስትክበት
ጨዋታዎች የትኞቹ ናቸው?
ሙጂብ፡- ጎንደር ላይ
ከደቡብ ፖሊስ ባደረግነው
ጨዋታ በቃ አሸንፈናል
ብለን ርግጠኝነት በተሰማን
ሰዓት የተቆጠረብን ግብ
አቻ አድርጎናል በዚህም
በጣም ተበሳጭቻለሁ…
በ ማ ሸ ነ ፋ ች ን
የተደሰትኩበት ደግሞ
ጅማ አባጅፋርን 6ለ1
የረታንበት ጨዋታ ነው፡
፡ በዚህ ጨዋታ አራት
ግብ አስቆጥሬያለው
በውጤቱም ደረጃችንን
ማሻሻል በመቻላችን ደስተኛ ነበርኩ፡፡
ሀትሪክ፡- ተጨዋች በሆንክባቸው ክለቦች
ለአሰልጣኝ ገንዘብ ሰጥተህ ወይም ተጠይቀህ
አታውቅም?
ሙጂብ፡- በፍፁም ሰጥቼም አላውቅም
የጠየቀኝ አሰልጣኝም የለም፡፡ በዚህ በኩል
እድለኛ ነኝ የፈረምኩት አምነውብኝ ባናገሩኝ
አሠልጣኞች በመሆኑ ገንዘብ ለመክፈል
አልተገደድኩም፣ የማወራው የእውነቴን ነው
ገጥሞኝም አያውቅም፡
ሀትሪክ፡-የአመቱ ልፋት የሚወሰነው
ከስሁል ሽረ ጋር በሚደረግ ጨዋታ ነው ምን
ውጤት ይጠበቅ?
ሙጂብ፡- የጨዋታው ስሜት ከባድ
ነው… ከባድ ትግልም ይጠብቀናል እኛ ጋር
ያለው ስሜትና የሚጠበቀው የግድ ማሸነፍ
በመሆኑ ያንን ለማድረግ ተዘጋጅተናል ከፈጣሪ
ጋር እናሳካለን ብለን እናምናለን ግዴታ
ማሸነፍ የሚጠበቅብን ጨዋታ እንደመሆኑ
ለሜዳው ላይ ፍልሚያ ተዘጋጅተናል፡፡ 90
ደቂቃ ይለየናል ከባድ ስሜት ያለበት ጨዋታ
ነውና ማሸነፍ ዋንጫ ከማንሣት ጋር የተያያዘ
በመሆኑ የምንችለውን እናደርጋለን፡፡
ሀትሪክ፡- በጨዋታው በዳኛ ስህተት
ወይም በሌላ የውጪ ኃይል አሸናፊው
መታወቅ የሌለበት ጨዋታ ደስ ይላል ከዚህ
አንፃር ለሽሬው ጨዋታ ምን መደረግ አለበት
ትላለህ?
ሙጂብ፡- አሁን ያለው የኳሱ ሁኔታ
የሚታወቅ ነው ኳሱና ፖለቲካው አንድ
መሆኑ የኳሱ እድገት ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል
ያ ስሜት ስላለ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡ ትልቅ
ደርቢ እንደመሆኑና የዋንጫ ጨዋታ ስለሆነ
ጥንቃቄና ጥበቃ ያስፈለገዋል፡፡ ከባድ ጨዋታ
ነው ትልቅ ትርጉም ያለውም በመሆኑ
ፌዴሬሽኑ ትልቅ የቤት ሥራ አለበት፡፡
ጨዋታው በሠላም እንዲጠናቀቅ እመኛለው፡፡
ሀትሪክ፡-በሀገራችን እግር ኳስ ላይ
ዘረኝነቱ ተንሰራፍቷል እዚህ ላይ የምትለው
አለ?
ሙጂብ፡- እግር ኳስን ጨምሮ አጠቃላይ
ስፖርት ከዘረኝነት ነፃ የሆነ መድረክ ነው፡
፡ ብዙ ጊዜ የሚሰራው እንዲህ እንዲሆን
ነው በኛ ሀገር ግን አሁን ላይ ያለው ሁኔታ
ያስጠላል ዘረኝነቱ ኳሱ የሠላም መስበኪያ
መድረክ የሆነው እግር ኳሳችን ላይ ዘረኝነት
መንፀባረቁ አሳፋሪ ነው… ክለብ ሲደገፍም
ፖለቲካና ብሔርተኝነት ይንፀባረቅበታል
ከዚህ በኋላም ካልተስተካከለ አደጋ አለው
ደጋፊውም የኳሱ ባለድርሻም ከዘረኝነት ነፃ
ሆኖ ነው ኳስን መመልከት ያለበት፡፡
ሀትሪክ፡- ይሄ የዘረኝነቱን ችግር
ለማስወገድ የቀረበው ሃሳብ ፎርማቱ ይቀየር
የሚል ነው፡፡ ፎርማቱ ይቀየር ወይስ?
ሙጂብ፡- በፍፁም አልስማማም….
ፎርማቱ መቀየር የለበትም… በሀገር ደረጃ
ካለው ችግር አንፃር መታሰቡን እረዳለሁነገር ግን መፍትሔ አይሆንም ሁሉም ራሱን
የማረም ርምጃ ሲወስድ ብቻ መፍትሔው
የሚመጣው…. እንደ ተጨዋች ግን ፎርማቱ
ይቀየር በሚለው አልስማማም፡፡ የኳሱን
እድገት ከማቆሙም ውጪ ህዝብን ከህዝብ
የሚያራርቅ በመሆኑ ፎርማቱ ይቀየር
በሚለው አልስማማም፡፡ ፕሪሚየር ሊጉ
ባለበት ሆኖ የስፖርት ቤተሰቡንና ባለ ድርሻ
አካላት ማስተማርና መለወጥ የሚለው
መቅደም አለበት ባይነኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ክልል ወጥቶ ወይም ከሜዳ
ውጭ ማሸነፍ ከባድ ሆኗል…ይሄንንስ
እንዴት አየኸው?
ሙጂብ፡- የአቅም ማነስ ነው ብዬ
አላስብም፡፡ በእርግጥም የሚታይ ተፅዕኖ
ይኖረዋል፡፡ በተለይ የደጋፊ ተፅዕኖ ከባድ
ነው ከሜዳ ውጪ ስትጫወት ብዙ ተፅዕኖዎች
ስላሉ እንደ ሜዳህ መጫወት አትችልም
ሁኔታው ከባድ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ብዙዎች ከሜዳ ውጪ
ስንጫወት የዳኛ ተፅዕኖ አለ ይላሉ… አንተስ?
ሙጂብ፡- በርግጥ ተፅዕኖ አለ…. የዘንድሮ
ፕሪሚየር ሊግ ከበድ ያለ ቢሆንም ያንን
ተቋቁመው እዚህ ደረጃ መድረሳቸው ጥሩ
ነው… ተፅዕኖው እንዳለባቸው ግን ይገባኛል
በየሜዳው ያለው የደጋፊ ተፅዕኖ የስፖርታዊ
ጨዋነት ችግር ተቋቁመው ማጫወታቸው
ግን እንደእኔ ትልቅ ነገር ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ፋሲል ከነማ በጨዋታው
ተበልጦ ሳይሆን በዳኛ ስህተት የተሸነፈበት
ግጥሚያ አለ?
ሙጂብ፡- እርሱማ አይጠፋም.. ሀዋሳ
ላይ በነበረን ጨዋታ የፌር ፕሌይ ግብ
ተቆጥሮብናል፡፡ ያንን ጨዋታ አሸንፈን ቢሆን
ኖሮ የተሻለ ነጥብ ይኖረን ነበር በዚያ ቅር
ብሎኛል፡፡
ሀትሪክ፡- የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች
ድጋፍንስ እንዴት ትገልፀዋለህ?
ሙጂብ፡- ደጋፊዎቻችን በክለባቸው
የማይደራደሩ ጠንካሮች ናቸው የነርሱ ጥንካሬ
ነው እዚህ ደረጃ ላይ ያደረሰን… ከጀርባችን
ሁሌ የማይጠፉ ለክለባቸውና ለተጨዋቾቹ
ያላቸው ክብርና ፍቅር የሚያስደስት ነው
ምርጥ ደጋፊዎችን ስለያዝን ደስተኞች ነን…
ሀትሪክ፡- ከ15ቱ የሊጉ ክለቦች መሃል
የፋሲል ከነማ የተለየ መገለጫ የትኛው ነው?
ሙጂብ፡- አሰልጣኛችን ውበቱ አባተ
የሚታወቀው ኳስን መሰረት አድርጎ
በመጫወቱ ነው፡፡ ያንን ነገር ነው የሰራነው..
ቡድናችን በይበልጥ ኳስን ተቆጣጥሮ
የሚጫወት ቡድን ነው ቶሎ ቶሎ ወደ
ግብ ይደርሳል ብዙ ግብ ነው እያስቆጠርን
የነበረው… በተለይ ከ2ኛ ዙር በኋላ በይበልጥ
የማጥቃት አቅማችን እንደ ቡድን ምርጥ
ነው… ይሄ ነው ልዩነታችን፡፡
ሀትሪክ፡- ፋሲል ከነማን የመረጥከው
ብቸኛ የጠየቀህ ክለብ እሱ ስለሆነ ነው?
ሙጂብ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ
ቡናና መከላከያ አናግረውኛል… ነገር ግን
ምርጫዬ ፋሲል ስለነበር ወደዚያ አቅንቻለሁኝ
በዚህ ደግሞ ደስተኛ ነኝ፡፡
ሀትሪክ፡- የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ትልቅ
አቅም የምትለው ምኑን ነው?
ሙጂብ፡-አሰልጣኝ ውበቱ ያለው አቅም
የሚታወቅ ነው ምንም ጥርጥር የለውም
በሚገባ ታታሪ የሆነ አሰልጣኝ ነው ቡድኑን
ጠንካራ የማድረግ አቅሙ በግል ከተጨዋች
የሚፈልገውን ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት
ልዩ መለያው ነው፡፡ ጠንካራ አሰልጣኝ
በመሆኑ ቡድኑን ጠንካራ አድርጎታል
በአሰልጣኛችን ደስተኛ ነኝ፡፡
ሀትሪክ፡-ያንተ ምርጡ አሰልጣኝ ማነው?
ሙጂብ፡- አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ነዋ….
ይሄማ ጥርጥር የለውም፡፡
ሀትሪክ፡-አሁን እያሰለጠነህ ስለሆነ
ፈርተህ ነው?
ሙጂብ፡- (ሳቅ በሳቅ) በፍፁም አይደለም
ሀዋሳ እያለሁ አሰልጥኖኛል እዚህም አብረን
ነን ለኔ ምርጡ እርሱ ነው፡፡
ሀትሪክ፡-በፋሲል ደጋፊዎች ትወደዳለህ…
ይገባኛል የሚል አቋም አለህ…?
ሙጂብ፡- (ሣቅ) የመውደዱ ነገር
የደጋፊው እይታ ይመስለኛል… እኔ ስራዬን
በታማኝነት መስራት ነው የሚጠበቅብኝ…
ደጋፊው ሊጠላህም ሊወድህም ይችለል፡
፡ በእርግጥ ደጋፊ ከሚጠላህ ቢወድህ
ይመረጣለና በደጋፊዎቹ በመወደዴ ደስተኛ
ነኝ፡፡ የደጋፊ ጫና ከባድ ነው ሀዋሳ
እያለሁ ይሄ ነገር አጋጥሞኝ እንደምንም
ተቋቁሜዋለው እዚህ ፋሲል ከነማ ግን ድጋፍ
እንጂ ጫና የለብኝም፡፡
ሀትሪክ፡-አብሬው ብጫወት ደስ ይለኛል
የምትለው ተጨዋች ማነው?
ሙጂብ፡- አሁኝ የለም … በፊት ግን
ከሙሉጌታ ምህረት ጋር የመጫወት ህልም
ነበረኝ… ኳስ ሊያቆም አካባቢ ከርሱ ጋር
ተጫውቼ ፍላጎቴን አሳክቻለሁ፡፡
ሀትሪክ፡-የፋሲል ከነማ የቡድን አጋርህ
አይናለም ኃይለ ውድድሩ ፕሪሚየር ሊግ
አይባል የረብሻ ወይም የድብድብ ሊግ ይባል
ሲል ባለው ሁኔታ ቅሬታውን ገልጿል…
ሙጂብስ ምን ይላል?
ሙጂብ፡- (ሳቅ በሳቅ)
አዎ እውነቱን ነው…
ከባድ ነው… አሁን
ያለው ሁኔታ
ያሰጋል… አይናለም
እንዳለው ሁኔታው
ያስጠላል ክለቦች
በምን አይነት
መልኩ ውጤት
እ ን ደ ሚ ያ መ ጡ
እየሰማንና እያየን ነው፡፡
ደጋፊዎች ውጤት እያስለወጡ
ነው… ዘረኝነቱ ሰፍቷል…
እውነት ነው ሊጉ ከጨዋታ
ይልቅ የረብሻ ሊግ ነው ቢባል
ነው የሚቀለው…የምናየው
መጥፎ ሁኔታ እንዲስተካከልና
ሠላም እንዲሆን እመኛለው
በዚህ ከቀጠለ ግን ለኳሱ
ከባድ አደጋ ነው የተሻለና
ጥሩ ጊዜ እንዲመጣ ተስፋ
አደርጋለው፡፡
ሀትሪክ፡- ጠቅላይ
ሚኒስትር ዶ/ር አብይ
አህመድ በሌለ ኳስ ላይ
ረብሻው ከቀጠለ ድብድቡ
ካልቆመ እጃችንን
እንሰበስባለን ሲሉ
ተናግረዋል.. ይሄስ
ስጋት አይፈጥርም?
ሙጂብ፡-
በርግጥ ኳሱ ገና ነው
ገና ብዙ የሚቀሩት
ጉዳዮች አሉ…
የደጋፊዎች የእርስ
በርስ ድብድብ
ለሰው ልጆች
ህልፈት ምክንያት
እየሆነ ነው በዚያ
ላይ ኳሱ አለማደጉ
በራሱ ያበሳጫል…
በጣም ከባድ ችግር
ነው፡፡ ሁኔታው
ከቀጠለ ለኳሱ
አደጋ ይሆናል ብዬ
እየሰጋው ነው፡፡
ሀትሪክ፡-ከ40 -60
ሚሊዮን ብር በአመት
እየወጣ ሽልማቱ 150 ሺ ብር
መሆኑ አይገርምም?
ሙጂብ፡- (ሣቅ) ሁሌ የማስበው
ነገር ነው፡፡ ሽልማቱ 150 ሺ ብር ሲባል
ያስቃልኮ.. ሁሌ ባወራው የምፈጥረው
ነገር ስለሌለ ለራሴ አውርቼ ነው ዝም
የምለው… በጣም የሚያሳዝን ነገር
ነው፡፡ ገንዘቡ ቀርቶ የክብር ሽልማት
ቢሰጥኮ ይሻላል… ገንዘቡ ምንም
ትርጉም የለውም ማሸነፍ ዋንጫ
መውሰድ ብቻ ነው ትርጉሙ.. ያንን
ሳስብ አፍራለው፡፡
ሀትሪክ፡- እድል ቢሰጥህ
ኢትዮጵያ ውስጥ መቀየር
ወይም ማድረግ የምትፈልገው
ምንድነው?
ሙጂብ፡- በየጊዜው
ባይሆንም በየሁለት
የአፍሪካ ዋንጫ ላይብንሳተፍ ደስ ይለኛል፡፡ ሰፊ ጊዜ እየተቆጠረ
ከመድረኩ ከምንርቅ ሌላው ቢቀር በጥቂት
የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ብንገኝ ደስ ይለኛል ይሄ
ታሪክ ተቀይሮ ማየት እፈልጋለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ፕሮፌሽናል ተጨዋች የመሆን
እድል አግኝተህ ነበር.. እንዴት ነበር?
ሙጂብ፡- ለ25 ቀናት የሙከራ እድል
ሞርኮ ሄጄ ነበር…ሙከራው ባይሳካም
በቀጣይም እሞክራለው
ሀትሪክ፡-የሞሮኮና የኢትዮጵያን የኳስ
ልዩነት ታዘብክ?
ሙጂብ፡- በጣም ሰፊ የሆነ ልዩነትማ
አለ፡፡ አንገናኝም.. በቡድን አደረጃጀት፣
በስታዲየም ጥራት ሜዳ ላይ ባለው ስልጠና
ሰማይና ምድር ነን… በእውነት አንገናኝም
ይሄን ታዝቤያለው፡፡
ሀትሪክ፡-ለኢትዮጵያ ምን ትመኛለህ?
ሙጂብ፡- ያለ ጥርጥር ሠላምን እመ
ኛለው… ሠላም ለሁሉም ነገር ወሳኝ ነው
በተለይ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ዋና
ጉዳይ ነው…. ሠላም ከሌለ እንደ ሀገር እንደ
ዜጋ እንደ ተጨዋች መኖር አይቻልም
ኳሱም የሚኖረው ሠላም ሲመጣ ነው…
ያንን ሠላም ለማምጣት ሁሉም ኢትዮጵያዊ
ሊያስብበት ይገባል በተለይ ኳሱ ላይ ሠላም
እንዲመጣ የማድረግ አቅም ያለው ደጋፊው
ነው ተጨዋቹ 22 ሆኖ ነው ወደ ሜዳ
የሚገባው ከነርሱ ጀርባ ያለው ተመልካች ነው
ዋነኛ ባለድርሻ… እንደ ሀገር አሁን ያለውን
ሁኔታ ያሳስበኛል….ሠላም እንዲሆን ሀገሪቷ
እንድትረጋጋ እፀልያለው፡፡ ሀገሬን አላህ
ሠላም ያደርጋት ነው የምለው፡፡
ሀትሪክ፡- ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደልኮ
የተጨዋቾችም እጅ አለበት… ደጋፊ
የሚያነሳሱ ተጨዋቾች፣ አሰልጣኞች የቡድን
መሪዎች አሉ፤… እዚህ ላይ ምን ትላለህ?
ሙጂብ፡- አዎ ትክክል ነው ያ ግን
ከስሜታዊነት የሚመነጭ ይመስለኛል፡፡
ሁሉም ስሜቱን መቆጣጠር እንዳለበት ግን
አምናለሁ፡፡ የተጨዋቾች አንዳንድ ድርጊት
በርግጥም በተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎች ላይ
ተፅዕኖ ይፈጥራልና ሁሉም ባለድርሻ አካል
ስህተቱን ማረም አለበት ማለት እፈልጋለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- የሚከፈለው ደመወዝና የናንተ
የኳስ ደረጃ አይገናኝም…. ክፍያው በዝቷል
የሚሉ አሉ… ትስማማለህ?
ሙጂብ፡- አልስማማም… እንደተጨዋች
ሳየው ያንሳል ባይ ነኝ፡፡ እንደ ሀገሪቱ እግር
ኳስ ደረጃ ካየነው ግን ልዩነት አለው፡፡
አፍሪካም ውስጥም ያለው ነገር ተመሳሳይ
ነው ለምን የኛ እንደሚጋነን አልገባኝም፡፡
ሀትሪክ፡-ትዳር እንዴት ይዞሃል…. አሪፍ
ነው?
ሙጂብ፡- አሪፍ ትዳር አለኝ ባለቤቴ
ኢማን ስሩር ትባላለች… ትዳር ከመሰረትን
5 አመታችን ነው፡፡ ሲዳማ እያለሁ ነው
ያገባኋት… ደስተኛ መሆኔንንና እንደምወዳት
ልነግራት እፈልጋለው… በህይወቴ ላይ ከባድ
ተፅዕኖ ያሳረፈች ምርጥ ሚስቴ ናት፡፡
ሀትሪክ፡-ሲዳማ ቡናን በተቃራኒ
ገጥመህ ግብ አስቆጥረህ ታውቃለህ…
አስቆጥረህስ ጨፈርክ?
ሙጂብ፡- ተቃራኒ ሆኜ ገጥሜ
ግብ አስቆጥሬያለሁ ስሜቱ ከባድ
ነው…እያጠቁን በነበረበት
ሰዓት ያስቆጠርኩት ግብ
በመሆኑ ማሊያዬን አውልቄ
ጨፍሬያለሁ… በኋላ
ሳናግራቸው ቅር ብሏቸዋል
ለካ እንደዚህ ማድረግ
አልነበረብኝም አልኩ…
ግቧ ወሳኝ መሆኗን
ብቻ ነው ያሰብኩትና
የጨፈርኩት፡፡
ሀትሪክ፡-አሁን
ለነርሱ ጥሩ መመኘት
አይከብድህም?
ሙጂብ፡- (ሳቅ)
አሁንማ የዋንጫ
ተፋላሚ ናቸው የደርቢ
ተፋላሚያችን ናቸውኮ /
ሳቅ/
ሀትሪክ፡-ሙጂብ በምን
ዘና ይላል?
ሙጂብ፡- በፕሌይ
ስቴሽን… ፕሌይ ስቴሽን ደስ
ይለኛል፡፡
ሀትሪክ፡-ጨረስኩ..
የምታመሰግነው ሰው ካለ?
ሙጂብ፡- ውዷ ባለቤቴን ኢማንን በጣም
አመሰግናለሁ፡፡