በካፍ ቶታል ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል ውስጥ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የገባው ኢትዬጵያዊው ቅ.ጊዮርጊስ ከማማሎዲ ሰንዳዉንስ ጋር ላለበት የምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ ከነ በስቲያ ሐሙስ ማለዳ ወደ ደ.አፍሪካ ይጋዛል።በርካታ ክለባቸውን ለማበረታታት ወደ.አፍሪካ ለመሄድ ዝግጅት ቢያደርጉም ኤምባሲው በፈጠረባቸው አላስፈላጊ መስፈርቶችና ጥያቄዎች መጉላላታቸውና እንቅፋት እየተፈጠረባቸው መሆኑን በተለይ ለሀትሪክ ድረ-ገፅ ገለፁ።
በሌላ በኩል የቅ.ጊዮርጊስ ተጫዋቾች በአካል ኤምባሲ ድረስ ካልመጡ ኤምባሲው ቪዛ አልሰጥም በማለቱ የቡድኑ ተጫዋቾች ኤምባሲው ድረስ ለመሄድ ተገደዋል።
ከክለቡ ደጋፌዎች ከተገኘው መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው በርካታ ደጋፊዎች ወደ .አፍሪካ ተጉዘው ቡድናቸውን ለማበረታታት ፍላጎት ቢያሳዩም ኤምባሲው አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረጉ በርካታ ደጋፊዎች ከጉዞው መቅረታቸው ነው የተሰማው።
ከዚሁ ከቅ.ጊዮርጊስ ዜና ጋር በተያያዘ ከማማሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ላለባቸው ወሳኝ ጨዋታ ቡድኑ 18 ተጫዋቾችን ይዞ የሚጋዝ ሲሆን ሳላህዲን ሠይድ በሁለት ቢጫ፣በሐይሉ አሰፋ ቱሳ ምንተስኖት በጉዳትእ አብረው ከቡድኑ ጋር የማይጋዙ ሲሆን በጉዳት ምክንያት ለረዥም ጊዜ ከሜዳ ርቆ የነበረው ምን ያህል ተሾመ አብሮ ከቡድኑ ጋር የሚጓዝ መሆኑ ታውቋል።