በደሞዝ እና ጥቅማጥቅም ክፍያ ምክኒያት ከሲዳማው ጨዋታ መልስ ልምምድ ያቆሙት የጣናው ሞገድ ባህር ዳር ከነማ ተጫዋቾች ትናንት የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ልዑል ለሁሉም ተጫዋቾች ደሞዝ እንደሚገባላቸው የተናገሩ ቢሆንም ተጫዋቾቹ የገባላቸው ብር የአንድ ወር ብቻ መሆኑን በዚህም ደስተኛ እንዳልሆኑ እና የሶስት ወር ደሞዝ ካልገባልን ልምምድ አንጀምርም ማለታቸው ከጥቂት ስአታት በፊት በሰራነው ዜና አሳውቀናቹህ ነበር። አሁን ከባህርዳር የደረሰን መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ ደግሞ ተጫዋቾቹ ችግራቸው ተቀርፎ ወደ ልምምድ መመለሳቸውን ሀትሪክ ስፖርት ያገኘችው መረጃ ያመላክታል። ከወልዋሎ አዲግራት ጋር ላላቸው ጨዋታም ዝግጁ ሆነው እንደሚቀርቡም ተነግሯል።