ቅዱስ ጊዮርጊስ በዛሬው እለት አራት ተጫዋቾችን ማስፈረሙ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል፡፡
አብዱልከሪም መሃመድ ፤ጋዲሳ መብራቴ፤ለአለም ብርሃኑ፤ሙሉዓለም መስፍን
የቀኝ መስመር ተከላካዩ አብዱልከሪም መሃመድ ከኢትዮጵያ ቡና የክንፍ አጥቂው ጋዲሳ መብራቴ ከሐዋሳ ከተማ የአማካኝ ስፍራ ተጫዋቹ ሙሉዓለም መስፍን እና ግብ ጠባቂው ለአለም ብርሃኑ ከሲዳማ ቡና በዛሬው እለት ለሁለት አመት የሚያቆያቸውን ስምምነት ፈፅመዋል።
- ማሰታውቂያ -
አራቱም ተጫዋቾች ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለመጫወት በመፈረማቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።