“እግር ኳሱ ከግለሰቦች ጣልቃ
ገብነት ነፃ ሊሆን ይገባል”
- ማሰታውቂያ -
የሃዋሳ ከነማው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
ዋሊያዎቹ ሀዋሳ ላይ ጨዋታቸውን
ካደረጉ በኋላ የሃዋሳ እግር ኳስ ክለብ ሰዎችና
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲን ባሻህ
የሊግ ኮሚቴ ሰብሳቢው አቶ አበበ ገላጋይ ሃይሌ
ሪዞርት ላይ ተገናኙ፡፡ “የክለባችን የውስጥ
ችግርና ድክመት እንዳለ ሆኖ ይህንንም መረጃ
እዩልንና በምትችሉት አቅም እንዲስተካከል
አድርጉ ብለን ያሳየናቸው መረጃዎች ነበሩ፡
፡ ለውጥ ባይታይባቸውም አደባባይ ይዘን
ለመውጣት ግን አልቸኮልንም” ሲል የሃዋሳው
የመልበሻ ቤት አለቃ ውበቱ አባተ ለሀትሪክ
ገልጿል፡፡ “አሁን ግን መስመር እያለፈ መጣ፡
፡ የተላለፈው የ1 አመት እገዳና የ30ሺህ ብር
ቅጣት ፍትህ ያልሰፈነበት ነው”ሲል ይናገራል፡
፡ ዮሴፍ ከፈለኝ ስለተላለፈበት ቅጣትና ሌሎች
እግር ኳሳዊ ጉዳዮች የሃዋሳ ቡድን ካረፈበት
ሀራምቤ ሆቴል ተገኝቶ አሰልጣኝ ውበቱ
አባተን አነጋግሮታል፡፡
ሀትሪክ፡-በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ጃኮ አራፋት
ተጎዳ እንዴት ነው ጤናው?
ውበቱ፡- ከሜዳ ቀጥታ ወደ ቤተዛታ
ሆስፒታል ነው ያመራው፡፡ አፍንጫው ላይ
የመሰበር ጉዳት ገጥሞት ዛሬ ጠዋት ደግሞ
ለመታየት ሄዷል፡፡ ጨዋታው ላይ ዳኛው ዝም
ያሉት አጠገቡ ስለነበሩ ጉዳቱ አይጎዳውም
ብለው አስበው ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጉዳቶች
ወዲያው ላይታወቁ ይችላሉ፡፡ ጨዋታውን
ትሪቩን ሆኜ ነበር ያየሁት ወደሜዳ ሳይመለስ
በመቅረቱ ጉዳቱ ከፍ እንዳለ ገምቻለሁ
(ቃለምልልሱ ቅዳሜ ጠዋት የተሰራ ነው)
ሀትሪክ፡- ይግባኙ ሳይመለስ ግን ቅጣቱ
መጀመሩ ተገቢ ነው?
ውበቱ፡- በይግባኝ ያለ ጉዳይ ምላሽ
እስካላገኘ ድረስ የተቀጣው ሰው ጨዋታው
ላይ መቀጠሉ አይቀርም፡፡ እንደክለብም
ይግባኝ አስገብተናል፡፡ ርግጠኛ ለመሆን ስንል
እንጂ የሚከለክለኝ ህግ ያለ አይመስለኝም፡፡
ሀትሪክ፡- አንተ የተቀጣኸው ድሬ ላይ
የተካሄደውን የድሬደዋና የሃዋሳ ጨዋታ ተከትሎ
ነው እስቲ ትክክለኛውን ሂደት አስረዳን?
ውበቱ፡- የተወሰነውን ቅጣት የሚሰማ
ሰው ሜዳው ተረብሾና ሁከት ተፈጥሮ የሆነ
አደጋ የደረሰ ነው የሚመስለው ግን በፍፁም
የተከሰተ ችግር የለም፡፡ ድሬዎች በሜዳው
ሆነ ከሜዳ ውጪ ጥሩ አቀባበልና አሸኛኘት
አድርገውልናል፡፡ ቅጣቱ ግን ሜዳው ላይ
የነበረውን ነገር አይገልፀውም፡፡ ዳኝነቱን
በተመለከተ ተደጋጋሚ ጊዜ ተቃውሞዬን
መግለፄ ለዳኛው አልተመቸው ይሆናል፡
፡ ተቃውሞ እንድናሰማ ያደረጉን በርካታ
ነገሮች ግን ነበሩ፡፡ ለቅጣት መነሻ የነበረው
የፍፁም ቅጣት ምት ተሰጠብን፡፡ ባናምንበትም
ኳሱ ተመታና ገባ፡፡ ከመሃል ሜዳ ሊጀመር
ሲል ኳሱ ይውጣና የቴክኒክ ክስ እናስይዝ
ስል ዳኛው ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ይህ ህጉ
የሚሰጠን መብት በመሆኑ ዳኛው ሊለውጠው
የሚችለው ነገር የለም፡፡ በዚህ የተነሳ ተቃውሞ
ሳሰማ ከሜዳ ውጣ አለኝ፡፡ እሺ እወጣለሁ
ነገር ግን ጨዋታው የሚቀጥለው ክሱ ከተያዘ
በኋላ ነው ብዬ ለምክትል አሰልጣኝ ሙሉጌታ
ምህረት ነግሬው ወጣሁ፡፡ በዚህ ላይ በርካታ
ስሜታዊ የሚያደርጉ ውሳኔዎች ነበሩ፡፡ ያም
ሆኖ ውሳኔዎቹ እንደግል እይታ ሲወሰን
ይችላል፡፡ ፋውል ነው አይደለም ሪጎሬ ነው
አይደለም የሚለው የዳኛው እይታ ሊወስነው
ይችላል፡፡ የቴክኒክ ክስ በማስያዝ ጉዳይ ግን
የዳኛው እይታ ከግምት የሚገባ አይደለም፡፡
ውጪ የነበረውን ኳስ የድሬደዋ ተጨዋቾች
በእጅ ውርወራ ሊጀምሩት ሲሉ ዳኛውን
አስቁምልን ክስ ማስያዝ እንፈልጋለን ስለው
አይቻልም አለ፡፡ ይሄን ማድረግ መብት አለው
ብዬ ግን አላስብም፡፡ አይቻልም ካለንኮ ሌላ ክስ
ልንከስ ነው ማለት ነው ያበሳጨንና ስሜታዊ
ያደረገን ውሳኔዎቹ ተገቢ አለመሆናቸው
አንፃር ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የስራ አስፈፃሚ ተሳድቧል ይላይ
ክሱ…… እውነት ተሳድበሃል? አመራሮቹ በቦታው
እንደሌሉ መረጃው አለኝና ስድቡ በተልዕኮ ነው
እንዴ?
ውበቱ፡- ይህን በምን ማረጋገጥ
እንደሚቻል አላውቅም፡፡ በርግጥ ጨዋታው
ይጀመር ሲል ክስ ሳናሲዝ አይቻልም ብለን
ከእለቱ ዳኛና ኮሚሽነር ጋር ተነጋገረናል፡፡
እንዴት እንደተረጎመውና በምን ጋር አያይዞ
ሪፖርት እንዳደረገ አላውቅም፡፡ በፍፁም
ግን ማንንም አመራር አልተሳደብኩም፡፡
የተወሰኑትን ነው የማውቀው ከነርሱ ጋር
ያለኝም ግንኙነት የታላቅና የታናሽ ነው፡፡
የበለጠ ቅርበትም ሆነ ጥላቻ የለኝም፡፡
ሀትሪክ፡- በዲሲፕሊን ውሳኔ ተከሳሽ
ለተከሰሰበት ጉዳይ ምላሽ ሳይሰጥ መወሰኑ
የተደበቀ ምክንያት ይኖራል አያስብልም?
ውበቱ፡- ምክንያቱም የሚያወቁት
ወሳኞቹ ናቸው፡፡ እኔ ግን እንደመብት ጥፋቱን
አድርጌው ቢሆን እንኳን አንድ አመት
(የመጨረሻው የቅጣት እርከን) ሲቀጡኝና 30
ሺህ ብር ክፈል ሲሉኝ ስለድርጊቱ መጠየቅ
እንደነበረብኝ ይሰማኛል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ውሳኔ
ሰጪዎችን መምከር አለብኝ ብዬ አላስብም፡፡
ይሄ ከፍተኛ ስህተት ነው፡፡ እንደሰው ራሴን
የመከላከል መብት አለኝ ይሄ ህገመንግስታዊ
ይመስለኛል፡፡
ሀ ትሪክ፡- አንዳንድ መረጃዎች ዲሲፕሊን
ኮሚቴ የቀጣው አምስት ጨዋታ እንጂ አንድ
አመት አይደለም እያሉ ነው መሃል ላይ ፋውል
የሰራ ሰው አለ እየተባለ ነውና መረጃው ደርሶሃል?
ውበቱ፡- ወሬውን ሰምቻለሁ፡፡ እንዲ
ያውም ብዙ ነገሮችን እንዳስብ አድርጎኛል፡፡
የሆነ የተምታታ ነገር እንዳለም ተሰምቶኛል፡፡
በቅርቡ ዳኞችን ሌቦች ጉበኞች ናችሁ ብሏል፡፡
ፍፁም ቅጣት ምት እንዳይመታ ተጨዋቾችን
አነሳስቷል የተባለ ሰው አምስት ጨዋታና 4
ሺህ ብር ቀጣን ይላል፡፡ ዳኞችን ተሳድቧል
ያለውን ውበቱን ግን አንድ አመትና 30 ሺህ
ብር መቅጣቱን ሳይ ያለው የዲሲፕሊን ኮሚቴ
ሁለት ነው ወይ የሚያስብል ነው፡፡ ጠርተው
ያላናገሩኝስ አንድ አመት የሚለው ውሳኔ
የነርሱ ስላልሆነ ነው ወይ ብዬ እንዳስብም
አድርጎኛል፡፡ እግር ኳሱ ከግለሰቦች ጣልቃ
ገብነት ነፃ ሊሆን ይገባል፡፡ የሚያድገውም
ያኔ ነው፡፡ ለማንኛውም ይግባኝ ብለናል፡፡ ይሄ
መብት ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ መብት ውጪ
ሌላ የተዘለለ መብት አለ፡፡ ለምን እንዲህ
አደረግክ ተብዬ አለመጠየቄ የተዘለለ መብቴ
ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ላይ
የተምታታ ነገር ያለ ይመስላል እንዴ?
ውበቱ፡- በማህተም ተደግፎ የመጣውን
ደብዳቤ ባምንም ለከባድ ጥፋት አምስት
ጨዋታና አራት ሺህ ብር የወሰነ የዲሲፕሊን
ኮሚቴ እኔ ላይ አንድ አመትና 30 ሺህ ብር
ይወስናል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሌላ አይነት
ችግር ካልተፈጠረ በስተቀር፡፡ በሁለት ፊትም
ያየናል ብዬም አላምንም፡፡ ምናልባት የተደበቀ
እጅ ሊኖር ይችላል እንጂ ዲሲፕሊን ኮሚቴ
ይህን ቀጥቶኛል ብዬ ለማመን ይከብደኛል፡፡
ሀትሪክ፡- 5 ጨዋታና 4 ሺህ ብር የሚያስቀጣ
ጥፋት አጥፍቻለሁ ብለህ ታምናለህ?
ውበቱ፡- እውነት ለመናገር ከሆነ እዚያ
ቦታ ላይ በነበረው ንትርክ ሶስት ጨዋታ
ተቀጥተሃል ቢባል ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
ዳኛው አስወጥቶኛል፡፡ ሪፖርቱንም ማክበር
ይኖርብኛል፡፡ ነገር ግን በዚህ መልኩ የተጋነነ
ጥፋት አድርጌያለሁ ብዬ አላምንም፡፡ ህዝብ
ለህዝብ ተጋጭቶ ድንጋይ ተወርውሮ፣
የፀጥታ ሃይል መጥቶ ከአቅም በላይ የሆኑ
ጨዋታዎች ላይ 4 እና 3 ጨዋታ እየተቀጡ
10 እና 20 ሺህ ብር እንዲከፍሉ እየተደረገ
በዚህ ጨዋታ ላይ ምንም ሳይፈጠር በሰላም
አልቆ የተወሰነው ውሳኔ በምንም መልኩ
ተቀባይነት ያለው አይደለም፡፡
ሀትሪክ፡- ለዚህ ጨዋታ አስቀድሞ የተመደበው
ኢንተርናሽናል አርቢትር ሃ/የሱስ ባዘዘው ነበር በኋላ
ላይ ነዉ ፌዴራል አርቢትር ዳዊት አሳምነው
እንዲያጫውት የተደረገው…. የተቀነባበረ ነገር
ያለ አይመስልም?
ውበቱ፡- በደንብ ሰምቻለሁ፡፡ እኛ ወደ
ድሬ ከተጓዝን በኋላ የክለባችን ፕሬዘዳንት
አቶ ታምሩ ታፌ ስልክ ደውለው ጨዋታውን
በጥንቃቄ እንድንወጣ፣ ተጨዋቾች አላግባብ
ቀይ አይተው እንዳይወጡና ቡድኑ እንዳይጎዳ
የተጋጣሚ ተጨዋች የፍፁም ቅጣት ምት
ክልላችን ውስጥ እንዳይገባ እንዲያደርጉ
ትዕግስት ተላብሰው እንዲጫወቱ መክረዋል፡
፡ የዳኛ ለውጥ አለ መባሉን ሰምቻለሁ፡፡
ይሄ የተደረገው ደግሞ ያለምክንያት ላይሆን
ይችላልና ተጠንቀቁ ብለውን ለተጨዋቾች
ነግሬያለሁ፡፡ መጨረሻው ግን እኔን በቀይ
ማባረር ሆነ፡፡ ሜዳው ላይ የሚያሳዝኑ እግር
ኳሳዊ የማይመስሉ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ ግልፅ
ሪጎሬ ተከልክለናል፣ ያለአግባብ የሆነ ቅጣት
ምቶች ተሰጥቶብናል፡፡ እግር ኳሳዊ ያልሆኑ
ህጎች ይፈፀሙ ነበር፡፡ ቅጣት ምት ሲመታብን
ለመከላከል ተጨዋቾቼ ሲደረደሩ ከከተማ
ውጪ እንድንወጣ ተደርገናል፡፡ 9 እርምጃ
የነበረው 18 እርምጃ ወደኋላ እንድናፈገፍግ
እንዲደረግ ነበር…. ይሄ ደግም የሰማነውን
መረጃ እንድናምን አድርጎናል፡፡
ሀትሪክ፡- የሃዋሳ ከተማ የዘንድሮው ደረጃ
ስንተኛ ሆኖ እንዲያጠናቅቅ አቅደሃል?
ውበቱ፡- አሁን ያለንበት ሁኔታ አስቸጋሪ
ነው፡፡ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ የነበረን አቋም
አላስደተኝም፡፡ ቅጣቱን ተከትሎም የተፈጠረ
ድባብ ይመስለኛል፡፡ ዘንድሮ ለእኛ ከባድ ገዜ
ነበር፡፡ አመቱ ሲጀምር የክለባችን ተጨዋች
የነበረውን ክብረ አብን በአደጋ አጥተናል፡፡
ከዚያ በኋላ አስቸጋሪ ጊዜ ለማሳለፍ ተገደናል፡
፡ አሁን ደግሞ ሌላ ችግር ተከስቷል ለኛ
ከባድ አመት ሆኖብናል፡፡ በቀጣይ ሁለት
ቀሪ ጨዋታዎች አሉን ጅማ ላይ ከጅማ
አባቡና ሐዋሳ ለይ ከመብራት ሃይል ጋር
እንጫወታለን፡፡ ሁለቱም ላለመውረድ
የሚጫወቱ እንደመሆናቸው ከባድ ትግል
ይጠብቀናል፡፡ አሁነ የደረጃ ጉዳይ ሳይሆን
ከመውረድ ስጋት ውጪ የመሆን እቅድ ይዘን
ነው የምንንቀሳቀሰው፡፡
ሀትሪክ፡- የዳኞች ምደባ ላይ ብዙ ጊዜ ቅሬታ
ይነሳልና ከምደባ አንፃር የምትለው ነገር አለ?
ውበቱ፡- አዎ ዳኞች ሲመደቡ ጥንቃቄ
መደረግ አለበት ባይ ነኝ፡፡ በውጪም አለምኮ
ዳኞች ለየጨዋታው ሲመረጡ ያላቸው
ብቃትና የጨዋታው ክብደት ይታያል
ውድድሩን የሚመሩት ኮሚሽነሮች ላይም
ትኩረት መደረግ አለበት ትልቅ ድርሻ
አላቸውና፡፡ አንድ ግጥሚያ በሃላፊነት ሲመሩ
ታማኝነት ይጠበቅባቸዋል የኛን ጨዋታ
ያየ ኮሚሽነር ለዳኛው የሰጠው ነጥብ ስንት
ይሆን? ያን የሚያውቀው እግዚአብሄር ብቻ
ነው፡፡ መዳቢዎቹ በዚህ በኩል መጠንቀቅ
አለባቸው፡፡ በተለይ ቀሪ ጨዋታዎች የክለቦች
የመቆየትና ያለመቆየት ህልውና የሚወስኑ
በመሆናቸው ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡
ሀትሪክ፡- ሃዋሳ በተደጋጋሚ ተበድሏል ማለት
ይቻላል?
ውበቱ፡- አዎ፡፡ ክለባችን አሁን
ያለበትን ደረጃ ሊቀይሩ የሚችሉ መረጃዎች
በእጃችን ላይ አሉ፡፡ እነሱን ይዘን ቸኩለን
አደባባይ መውጣት አላስፈለገንም፡፡ ድሬ
ላይ የተከሰተውም አይተን አልከሰስንም ፡፡
እግር ኳስ ነው ምንም ማድረግ አንችልም
ከነችግሩ መቀበል አለብን ብለን ነው ያለፍነው
እንጂ ተጎድተናል፡፡ በቀሪው ጨዋታዎች
መትረፍም ሆነ መውረድ እንደክለቦቹ ስራ
እንጂ በጀርባ ባለ ተንኮል መሆን የለበትም፡
፡ አመቱ ሲጀመር አንድ ቡድን ዋንጫ ሲበላ
ሶስት ቡድን ይወርዳል፡፡ ይሄ መሆን ያለበት
ደግሞ በየክለቦቹ አቅምና አግባብ ታይቶ
መሆን አለበት፡፡
ሀትሪክ፡- ውበቱን በህይወቱ ሁሌ የሚ
ገርመው ምንድነው?
ውበቱ፡- (ሳቅ) ሁልጊዜ ቀና ያልሆነ
ድርጊት ስመለከት ሰው እንዴት ይህን
ለማድረግ ህሊናው ፈቀደለት ብዬ እገረማለሁ፡
፡ ሰውስ ለምንድነው እንዲህ የሚጨክነው
ብዬ አስባለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- በሃዋሳ ውስጥ ክስተት የምትለው
ተጨዋች አጋጥሞሃል?
ውበቱ፡- በሐዋሳ ውስጥ እነ ፍሬው
ሰለሞን(ጣቁሩ) ፣ዳንኤል ደርቤና ጋዲሳን
በምሳሌነት መጥቀስ እችላለሁ፡፡ ከሁሉም
ከሁሉም ግን ከታች ያሳደግነው መሳይ
እያደረገ ያለው ነገር አስገራሚ ሆኖብኛል፡፡
ለቀጣይም ተስፋ እንድጥልበት አድርጎኛል፡፡
ሀትሪክ፡- የአሰልጣኞች ስንብት በዝቷል አንተስ
የስራ መሰናበት ስጋት የለብህም?
ውበቱ፡- የአሰልጣኞች ስንብት መቼ
እንደሚከሰት አይታወቅም፡፡ እንደሌሎቹ
ስራዎች አይደለም ስራው ላይ ለመቆየት
ምንም ዋስትና የለም፡፡ ምናልባት
ከተሰናበትኩኝ እንዲህ ታደርጋላችሁ ብለህ
ውልህ ላይ ታካትት ይሆናል፡፡ መሰናበቱ
ግን በየትኛውም አጋጣሚ ሊመጣ ይችላል፡
፡ ደደቢትን ይዤ 16 ጨዋታ አልተሸነፍኩም
እስከ 21ኛ ሳምንት ድረስ ሊጉን እየመራን ነው
ይሄ ሁሉ ከታች መጥተን ያሳካነው ስኬት
ነው፡፡ 22ኛ ሳምንት ላይ ግን በመሰናበቴ
ቡድኑን አልመራሁም፡፡ ክለቦች ግን እንዲህ
ባይቸኩሉ ተረጋግተው ለአሰልጣኞች እድል
ቢሰጡ ለአገርም ለክለብም ለባለሙያውም
ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ በተለይ ዘንድሮ ግን
በርካታ ስንብት አይተናል ይሄ ባይሆን
ጥሩ ይመስለኛል፡፡ከአመራሮቹ ጋር በሰከነ
ሁኔታ ቁጭ ብለን ችግሩ የት ጋር እንደሆነ
መርምረን፣ 2ኛ ዙር ላይ አንድ ተጨዋች ብቻ
አስፈርመን ቡድኑን የተሻለ ደረጃ አድርሰናል፡
፡ እየሰራን ያለነው ስራ ከግንዛቤ የከተቱ
በማስተዋል የሚመሩ አመራሮች ስለነበሩ
ምንም ስጋት አልነበረኝም፡፡
ሀትሪክ፡- ለተጨዋቾች የሚከፈለው ክፍያና
የጨዋታ ብቃት በጣም መራራቁን ለመግለፅ አንድ
ኪሎ ስኳር 100 ሺህ ብር መግዛት ነው የሚል
ወዳጅ ገጥሞኛል ውበቱስ ምን ይላል?
ውበቱ፡- ሁሉ ነገር እንደእዕይታ ይለ
ያያል፡፡ በኔ በኩል ግን ኳሱ የተለ ቦታ ላይ
አለ ብዬ አስባለሁ፡፡ ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾችን
በየክለቡ እያየን ነው ከየክለቦቹ በየቦታው
የሚመረጡ ተጨዋቾችን ስናይ አማራጮች
አሉን፡፡ በዘመንህ አንድ ጥሩ አጥቂ ላይኖር
ይችላል፡፡ አሁን ግን ሳላህዲን ሰይድ፣ ጌታነህ
ከበደ፣ ኡመድ ኡኩሪና አዲስ ግደይን በአንድ
ትውልድ ውስጥ ማግኘት የኳስ ጥሩ ጎን
ይመስለኛል፡፡
በርግጥ ሌሎች የደረሱበት ደርሰናል
ማለት ባይሆንም ከትላንቱ ዛሬ ሻል የሚል
ነገር እንዳለ ይሰማኛል፡፡ የሐዋሳ ጨዋታ
አይተው መንገድ ለይ አስቁመውኝ እንዲህ
አይነት ጨዋታ በኛ አገር አለ እንዴ? ካሁን
በኋላ ዲ ኤስ ቲቪን ትተን ወደ ወደስቴድየም
እንመጣለን የሚሉኝ ሰዎች ገጥመውኛል፡፡
ክፍያውና የተጨዋቾች አቅም የሆነ ደረጃ ላይ
የተመጣጠነ ሊሆን ቢችልም በጋራ መፈረጅ
ግን አይደገፍም፡፡
ሳላህዲን እዚህ የሚከፈለውን ባትከፍለው
ሌላ ጋር ሄዶ ይከፈለዋል፡፡ እኔም እዚህ
የሚከፈለውን ባላገኝ ከአገር ውጪ ወጥቼ
ሰርቼ ሊከፈለኝ ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ስናየው
ግን አባባሉ የተጋነነ ይመስለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- ዋልያዎቹን የመያዝ እቅድ አለህ?
በኛ አገር የምርጫ ሲስተምስ የሚሳካ ይመስልሃል?
ውበቱ፡- እኔ በጣም ርግጠኛ ነኝ ከፈጣሪ
ጋር አገሬን ለማገልገል እድል አገኛለሁ፡፡
ጊዜህ ነው ሰአቱ ያንተ ነው ብሎ ፈጣሪ ያለ
እለት ያኔ ዋልያዎቹን የምመራ ይመስለኛል፡
፡ ያኔም አገሬን ለማገልገል ፈቃደኛና ደስተኛ
እሆናለሁ፡፡ ረጅም ጊዜ ፈልጌው ለእኔ
አልሆንም የሆነ ወቅት ግን ይህ እድል
እንደሚመጣ ርግጠኛ ነኝ፡፡