ዘወትር ማክሰኞ ጠዋት ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ተናፋቂዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደልማዷ ሁሉ ነገም ከእናንተ ውድ አንባቢዎቿና ደምበኞቿ ጋር ለመገናኘት ስራዋን አጠናቃ ወደ ማተሚያ ቤት አምርታለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ከምርጥ ምርጥ ዘገባዎቿም ጋር ነገ እናንተን ስታገኝ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ሰፊና የሚወዷቸውን መረጃዎችን ይዛሎት የቀረበች ሲሆን በሀገር ውስጥ ልታስነብቦት ከተዘጋጀችባቸው መረጃዎቿ መካከልም በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን እያተረፈ በሚገኘው “ዘ ቢግ ኢንተርቪው” አምድ ቃለ-ምልልሷ የሀትሪክ
ስፖርት ጋዜጣ ኤስኪዮቲቭ ኤዲተር የሆነው ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ከታዋቂው የቀድሞ አትሌትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ከነበረው ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ጋር ያደረገው አነጋጋሪ ቃለ-ምልልስ ይገኝበታል፡፡
ከቀረቡለት ጥያቄዎች መካከል በቅርቡ አትሌቶች በእሱ ላይ ስለወጡበት ሰልፍ፣ ከሜቴክ ጋር ስሙ እየተያያዘ ስላለበት ሁኔታ፣ በስሙ ስለተከፈተ የፌስ ቡክ አካውንት እና ሌሎችም ጠግባችሁ የማትጨርሱት ምልልሶች ቀርቦሎታል፡፡
ለመሆኑ ኃይሌ ከሀትሪክ ጋዜጣ ጋር ባደረገው የቃለ-ምልልስ ቆይታ ምን ብሎ ይሆን?
ከምላሾቹ ውስጥ፡-
-“ለሀገሬ እየለፋሁ ሰላማዊ ሰልፍ በእኔ ላይ መደረጉ የሞራል
ውድቀት አድርሶብኛል፤ ባዶነት እንዲሰማኝም አድርጓል”
– “ከሜቴክ ጋር በሙስና ልሰራ ቀርቶ አንዲት ብሎንም እንኳን አልተሻሻጥኩም”
– “ያልተባልኩት የለም፤ 7ኛው እስር ቤት ኃይሌ ሕንፃ ስር ተገኝቷልም ተብያለሁ”
ያለበትም የሚጠቀስ ነው፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ከኃይሌ ገብረስላሴ ቃለ-ምልልሶች ውጪም በሊጉ የ6ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ወደ ሐዋሳ ተጉዞ በሲዳማ ቡና ሽንፈትን ካስተናገደው የቅ/ጊዮርጊስ ተጨዋቾች መካከል ከአማካዩ ሙሉዓለም መስፍን እና በሜዳው ከወላይታ ድቻ ጋር ተጫውቶ ነጥብ ከተጋራው የኢትዮጵያ ቡናው ተከላካይ ቶማስ ስምረቱ ጋርም በጨዋታውና በቡድናቸው ዙሪያ አናግራቸው ምላሾቹን ተጨዋቾቹ ሰጥተዋል፡፡
ማክሰኞ ማክሰኞ ምርጥ ምርጥ ዘገባዎቿን ይዛሎት የምትቀርበው ጋዜጣችን በባህር ማዶ አምዷም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ላይ ስለተከናወኑ ጨዋታዎች ጥልቅ መረጃን የምታስነብቦት ሲሆን ከእነዚህም መካከል ሊቨርፑል የሊጉን መሪነት ስለጨበጠበትና አጥቂው መሐመድ ሳላም ሀትሪክ ስለመስራቱ፤ አርሰናልም በሉካስ ቶሬራ አማካኝነት ጣፋጯን ሶስት ነጥብ ስለማስመዝገቡና በሌሎች ጨዋታዎች ዙሪያም እናንተን በማስነበብ በዘገባው ልናስደስቶት ተዘጋጅተናል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ነገ ገበያ ላይ ስትውል በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የነገ እና የረቡዕ ጨዋታዎች ዙሪያም መረጃዎችን ይዛሎት ከተፍ ብላለች፡፡
ሀትሪክ የእርስዎ ናትና አታምልጦት
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል
የኃይሌ ገብረስላሴን ዝምታ የሰበረ አነጋጋሪ ቃለ-ምልልስ ነገ ለንባብ በምትበቃው ተወዳጇ እና ተናፋቂዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ላይ ይጠብቁ!
Hatricksport team