በ12ኛው ሳምንት መርሀግብር አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ሰበታ ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን አስተናግዶ በባለሜዳዎቹ 2-1 አሸናፊነት መጠናቀቅ በኋላ። የሰበታው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለመገናኛ ብዙሀን አስተያየታቸውን ሲሰጡ የሀድያ ሆሳዕናው አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ግን አስተያየት ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ሳናካትት ቀርተናል።
“ውጤቱ ያስፈልገን ነበር ውጤቱ መያዛችን ደግሞ ትልቅ ነገር ነው” (ውበቱ አባተ ሰበታ ከተማ)
ስለጨዋታው
- ማሰታውቂያ -
ከባድ ጨዋታ ነው። እነሱ በተከታታይ ነጥብ ጥለው ነው የመጡት። ከወራጅ ለመሸሽ ነው እተጫወቱ ያሉት። እኛም በድሬዳዋ ተሸንፈን ነው እና የመጣነው ጨዋታው ትንሽ ውጥረት የነበረው። ከዛውጭ የጨዋታ መደራረቦች አሉን በዚህም ተጫዋቾቼ ላይ ድክመት ይታያል። ሌላኛው የምንጠቀምብቸው ተጫዋቾች አልነበሩም። ውጤቱ ያስፈልገን ነበር ውጤቱ መያዛችን ደግሞ ትልቅ ነገር ነው።
የዘንድሮ ዕቅዳቹህ
የደረጃ ሰንጠሬዡን ስንመለከት ብዙም የተራራቀ ነገር የለውም። አቅም በሚፈቅደው ደረጃ እስከ መጨረሻ በጥሩ ውጤት መሄድ እንፈልጋለን። እንደ ቡድን የተሻሻሉ ነገሮች አሉ። አሁን ላይ ሆኜ ግን ስለመጨረሻው ቀን መናገር ከባድ ነው። ግን በዚህ አመት ከስጋት ነፃ የሆነ ቡድን ለመስራት ነው እጣርን ያለነው።