በስሑል ሽረዎች በላይነት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኃላ ሁለቱም አሰልጣኞች ሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ – ስሁል ሽረ
ስለጨዋታው
“የዛሬው ጨዋታ እንግዲህ ከመሪዎቹ ተርታ ላለመራቅ የዛሬው ሥስት ነጥብ በእጅጉ ያስፈልገን ነበር።ተሸንፈንም እንደ መምጣታችን በቀጣይም ከሜዳችን ውጪ እንደመጫወታችን መጠን በግድ ያስፈልገን ነበር።ከዛ ረገድ ምንፈልገውን ነገር አሳክተናል ማለት ይቻላል።በዚህ መልኩ በጣም ደስተኛ ነኝ።”
- ማሰታውቂያ -
ስለደሞዝ ጉዳይና ቡድኑን ልምምድ አለማሰራት
“ትክክል ነው የደሞዝ ጥያቄ አለው ነገር ግን ብቻውን ሳይሆን ትንሽ ከጉንፋን ጋር በተያያዘ የጎሮሮ ህመም ነበረኝ።ግን የደሞዝ ጥያቄ በሰፊው ተነጋግረን ስምምነት ላይ ደርሰናል።በነገው ዕለት ሙሉ ለሙሉ ይፈታል በሚል ተስፋ አርገን እንጠብቃለን።”
አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ – ሀዋሳ ከተማ
ስለጨዋታው
“ጨዋታው በሁሉ መልኩ ጥሩ ነው ማለት ይቻላል።የመጀመርያ 45 ደቂቃ ላይ በተወሰነ ሲጀመር አካባቢ ማጥቃት ውስጥ ገብተው ነበር ጥሩ ነበሩ ከዛ በኃላ እኛ የተሻልን ይመስለኛል።ጎል ሲገባብህ ትወጣልህ ወደ መጨረሻ አካባቢ የገቡብን ግቦች ጎል ለማግባት ነጥብ ለመያዝ ባደረግነው እንቅስቃሴ በሰዓቱ እነሱ በደንብ ተጠቅመውበታል።የጎሎቹ መብዛት ይህ እንቅስቃሴ የፈጠረው ነው።”