የአሰልጣኞች አስተያየት
ምክትል አሰልጣኝ አስቻለው ሀ/ሚካኤል አዳማ ከተማ
” ጨዋታውን እንዳያችሁት ተጭንን ለመጫወት ሞክረናል እንቅስቃሴያችንም ጥሩ ነበር ብዙ የጎል እድሎችን መፍጠር ችለናል በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ ነገር ግን ጎል ማግባት አልቻልንም።
የአጨራረስ ችግር አለብን ነገር ግን እስካሁን ሽንፈት አላስተናገድንም ከዚህ በኃላ ላሉብን ጨዋታዎች ችግራችንን ፈተን ተፎካካሪ ለመሆን እንሰራለን።”
- ማሰታውቂያ -
አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ጅማ አባጅፋር
“ጨዋታውን እንዳያችሁት ጥሩ ነበር በሁተኛው አጋማሽ በተለየ መልኩ ተጭነን ለመጫወት ሞክረናል የጎል እድሎችንም ፈጥረናል ።
እንደምታቁት ትሬይኒንግ ሙሉ ለሙሉ በተለያዩ ችግሮች አቁመን ነበር ለዚህ ጨዋታ የመጣነው ያም ሆኖ ልጆቼ የመጫወት ፍላጎታቸው በጣም አስደስቶኛል ያገኝነው ነጥብ በጣም አስፈላጊ ነው ።
የበረኛ ችግር የለብኝም ሁሉም አሪፍ ብቃት ላይ ነው ያሉት። “