በዮሴፍ ከፈለኝ
የኢትዮጵያ ቡና ምክትል አሰልጣኞች
መሀመድ ኢብራሂም (ኪንግ) እና ሃብተወልድ
ደስታ ከኃላፊነታቸው የተነሱበት መንገድ
አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
በዝውውር ገበያው እንደሚገባ
አልተንቀሳቀሰም የተባለው ኢትዮጵያ
ቡና የክለቡን የውስጥ ምስጢር በደንብ
የሚያውቁትን አሰልጣኞች ማሰናበቱ ለሌላ
የሽግግር ጊዜ እንዳይዳርገውና ከ2003 ወዲህ
ለመጀመሪያ ጊዜ የዋንጫ አሸናፊ የመሆን
ህልሙን እንዳያኮላሸው እያሰጋም ነው፡፡
ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ ባህር ዳር
ያቀኑት የክለቡ አባላት ለአመታዊ ውድድር
የሚጠበቅባቸውን ዝግጅት ከማድረግ ይልቅ
የአሠልጣኞቹን ስንብት ሰበብ እንዳይሆን
ለደጋፊዎቹ ስጋት ሆኗል፡፡ ሀትሪክ
ባገኘችው መረጃ አሰልጣኝ ዲዲየር ጎሜዝ
ዳሮሳ ሁለቱን ም/ል አሰልጣኞች መሀመድ
ኢብራሂም (ኪንግ) እና ሀብተወልድ ደስታን
አልፈልጋቸውም ማለታቸውን ተከትሎ ክለቡ
የአሠልጣኙን ሀሳብ በመቀበል አሰልጣኝ
መሐመድ ኢብራሂምን (ኪንግ) ሲያሰናብት
አሰልጣኝ ሀብተወልድ ደስታን የሴቶቹን
ቡድን እንዲያሰለጥን መመደቡ ታውቋል፡፡
ሀትሪክ የመረጃውን እውነትነት
ለማረጋገጥ ከክለቡ የቦርድ ፕሬዚዳንት መቶ
አለቃ ፈቃደ ማሞ ጋር ባደረገችው ቆይታ
“አሰልጣኙ ከሁለቱ ምክትሎች ጋር መቀጠል
አልፈልግም፡፡ በምፈልገው መንገድ እያገዙኝ
አይደለም በማለቱ ያለ ጣልቃ ገብነት ውሳኔውን
አክብረን ሸኝተናቸዋል” ሲሉ አረጋግጠዋል፡
፡ መቶ አለቃ እንደተናገሩት “የምስራው
ብቻዬን ነው እያገዙኝ አይደለም፡፡ በልምምድ
ሰዓት የደከሙትን ወደ ኋላ አቆይቼ ሳሰራ
እንኳን አብረውኝ ሊቆዩ አልቻሉም፡፡ ከሁለቱ
ምክትሎች መስዑድ መሀመድ ይበልጥብኛል
እርሱን ባገኘው ደስ ይለኝ ነበር” በማለት
ሪፖርት ማድረጉን አስረድተዋል፡፡
ም/አሰልጣኙ ኢብራሂም በበኩሉ
ለሀትሪክ ሲናገር “ለምን እንደተሰናበትኩ
አላውቅም አሰልጣኙም ክለቡም አልነገሩኝም
ለነገሩ በቅርቡ ነው ኮንትራቴን ያራዘምኩት፡
፡ መቶ አለቃ ለእኔ ጥሩ ስሜት አለው ችግሩ
ከአሰልጣኙ ይመስለኛል፡፡ ለዕረፍት ወደ ሀገሩ
ሲሄድኮ የሚፈልጋቸውን ተጨዋቾች አናግሬ
እንድጠብቀው ስራ ሰጥቶኝ ነው አሁን ምን
ሃሳቡን እንዳስቀየረው አላውቅም” ሲል መቶ
አለቃ ፈቃደም “ኮንትራቱን ያራዘምኩት
ምናልባት ሃሳቡን እንዲለውጥ እናግባባውና
አሰልጣኙ እዛው ይቆያል ብዬ ነው፡፡ ከሀገሩ
ሲመለስ ቁጣው ይበርድና ለውይይት በሩን
ይከፍታል ብለን ዝም አልን እንጂ የ2010
መርሃ ግብር አልቆ ወደ ሀገሩ ለዕረፍት
ሲሄድ ነው ም/ል አሰልጣኞቹን አልፈልግም
ብሎ የሄደው” ሲሉ ከአሰልጣኝ መሐመድ
ኢብራሂም መረጃ የሚጣረስ ምላሽ ሰጥተዋል፡
፡
“ብዙ የምናገረውና በመረጃ አስደግፌ
ለህዝብ ይፋ የማደርገው ጉድ አለኝ፡፡ አሁን
ለጊዜው መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞን እስካናግር
ድረስ የጠለቀ መረጃ መስጠት አልሻም፡፡
አርባ ምንጭና አዳማ ጋር ሄደን ስንጫወት
ከልጁና ከሚስቱ ጋር ሊዝናና ቀድሞ ነው
የሄደው ሁለቱን ጠንካራ ጨዋታዎች
ላይ ቡድኑን አዘጋጅቼ ከሄድኩ በኋላ ነው
የተቀላቀለን፡፡ አሁን አይችሉም የሚለው ያኔ
ለምን አምኖ ቡድኑን ሰጠን? ይሄ እውነታ
የለውም፡፡ አሰልጣኝ ዲዲየር ጉሜዝን
የመሰለ ውሸታም አሰልጣኝ አላየሁም”
ሲል ተሰናባቹ ም/ል አሰልጣኝ መሐመድ
ኢብራሂም ለሀትሪክ ገልጿል፡፡ “በየሚዲያው
አላገዙኝም ብቻዬን ነው የሰራሁት የሚለው
ተጨዋቾቹ እንዲሟሟቁ ለማድረግ 6 ደቂቃ
እየሰጠና እንዳሰራቸው እያደረገስ እንዴት
ሊገመግመን ይችላል?” ለቡና ከኔ በላይ
ሊጨነቅና ሊቆረቆር አይችሉም፡፡ የአሠልጣኙ
ሹመት አንደኛውን ምክንያት የሙያ ሽግግር
ለማድረግ ነው፡፡ አንድም ቀን ግን በዚህ በኩል
የመጣበትን አላማ ሲፈፅም አላየሁም፡፡ ሁሌ
እቅድህ ምንድነው ብዬው እንጂ ቀድሞውኑ
እቅዱን አስረድቶኝ አያውቅም፡፡ በተፈለገው
መንገድ ይታይ የአሰልጣኙ ድርጊት የሚደገፍ
አይደለም” ብሏል፡፡
ሀትሪክ ባገኘችው መረጃ የክለቡ በረኛ
ሀሪሰን ሀትሱ ስንብት የመጣው ከአሰልጣኙ
ጋር ከተጋጨ በኋላ ነው፡፡ ሀሪሰን አሰልጣኝ
ዲዲዬ ጎሜዝ ችግር እንዳለበት፣ ከእርሱ
አጠገብ ሆኖ እንደማያውቅ፣ በተጨዋችነት
ዘመንህ በረኛ ብትሆንም አንድም ቀን
አበረታተኸኝ መክረኸኝ አታውቅም
ተጨዋቾችን ትከፋፍላለህ ብሎት በመናገሩ
ከክለቡ ጋር መለያየቱ ታውቋል፡፡
በፈረንሣዊው አሰልጣኝ ምርጫ
የአሰልጣኝ አስራት አባተና የአሰልጣኝ
እስማኤል አቡበከርን ሲቪ፣ ውጤትና
የስልጠና ሂደት ከተመለከተ በኋላ
አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር የክለቡ ም/ል
አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙን መቶ አለቃ ፈቃደ
አረጋግጠዋል፡፡
“አሁን የተለየ መናገር የምፈልገው ነገር
የለም ምናልባት መናገር ያለብኝ ቀን ሲመጣ
ብዙ ነገር እገልፅ ይሆናል፡፡ ክለቡ በዝውውር
ገበያው ፕላን ኤ እና ቢ ሊኖርው ይገባ ነበር
አሰልጣኙ ግን አልነበረውም የምንፈልጋቸው
ተጨዋቾች ቅ/ጊዮርጊስ ፋሲል ከተማና ሌሎች
ክለቦች ገቡ ከኛ የተሻለ ነገር ካገኙ ወደ ሌሎች
ክለቦች ሊገቡ እንደሚችሉ ማሰብ ነበረበት፤
ያዘጋጀው እቅድ ግን የለም” ያለው አሰልጣኝ
መሐመድ “አሁን ለቡና ከባድ ጊዜ ነው በጥሎ
ማለፉ ውድድር ውል ያላቸውና ከታዳጊዎች
ያሳደጋቸውን ይዞ ነው የሚገባው፤ ይሄ
ደግሞ ለኢትዮጵያ ቡና ቀጣይ ጉዞ ሊያስችግር
ይችላል” ሲል ስጋቱን ገልጿል፡፡
“ከሁሉ ግን የገረመኝ ሪፖርቱ ላይ ዩ.ቲዩብ
አያዩም ብሎ ከሶናል ይሄ ደግሞ አሰልጣኙ
የዩቲዩብ አፍቃሪ መሆኑን ያሳያል በኔ እምነት
የቡና ችግር በዩ.ቲዩብ የምንፈታው አይደለም፡
፡ በዩ.ቲዩብ መረጃ ቡናን ጠንካራ ማድረግ
ይቻላል ብዬም አላምንም” ሲል ሁኔታውን
ያስረዳው ተሰናባቹ አሰልጣኝ መሐመድ
“አሠልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝ ዩ.ቲዩብ እያየ
መጥቶ ያሰለጥናል እኔ ደግሞ ቡናን በዩ.ቲዩብ
ማሰልጠን አልፈልግም” ሲል የተገረመበትን
ሂደት አስረድቷል፡፡
ሀትሪክ ባላት መረጃ ከቡድኑ አባላት ጋር
ባለው ግንኙነት፤ የስነ ልቦና ድጋፍ የመስጠት
ሂደት ላይ ተጨዋቾቹን እንዴት ማናገር
እንዳለበት ሳይቀር 80 በመቶ የሚናገረው
አሰልጣኝ መሐመድ መሆኑ ታውቋል፡፡ “ለቡና
ሁሉ ነገሬን ለመስጠት ተዘጋጅቼ ነበር አሁን
በሆነው ነገር አዝኛለሁ” በማለት የተሰማውን
ቅሬታ አስረድቷል፡፡ የክለቡ ሌላኛው አሰልጣኝ
ሀብተወልድ ደስታ በበኩሉ ለሀትሪክ ሲናገር
“ለምን እንደተሰናበትን ምንም መረጃ የለንም፡፡
በግሌ ግን የሴት ቡድኑን እንዳደራጅ መመሪያ
ተሰጥቶኝ እየሰራሁ ነው የምገኘው” ሲል
መልሷል፡፡